“ህገወጡ የህወሀት ቡድንና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት ሊፈረጅ ይገባል” አብመድ ያነጋገራቸው የጎንደር  ከተማነዋሪዎች እና የህግ ምሁር ባሕር ዳር፡  ኅዳር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) ህገወጡ…

“ህገወጡ የህወሀት ቡድንና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት ሊፈረጅ ይገባል” አብመድ ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማነዋሪዎች እና የህግ ምሁር ባሕር ዳር፡ ኅዳር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) ህገወጡ…

“ህገወጡ የህወሀት ቡድንና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኝነት ሊፈረጅ ይገባል” አብመድ ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማነዋሪዎች እና የህግ ምሁር ባሕር ዳር፡ ኅዳር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) ህገወጡ የህወሀት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ በሚፈጽሙት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አለማቀፉ ማህበረሰብ በሽብርተኝነት እንዲፈርጃቸው ማድረግ እንደሚገባ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና የህግ ምሁር አስገንዝበዋል፡፡ ህገወጡ የህወሀት ቡድንም ይሁን ተልዕኮ ተቀባዩ ኦነግ ሽኔ ባለፉት አመታት አንድም በእጅ አዙር ሌላ ጊዜ ደግሞ በቀጥታ ሰዎችን ለጉዳት ሲዳርጉ ቆይተዋል፡፡ ቡድኖቹ የሽብር ስራን በንጹሀን ዜጎች ላይ ሲፈጽሙና ዘር የለየ ጥቃት ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ በመሆኑም እነዚህ ህገወጥ ቡድኖች በአለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሽብርተኛ ተብለው እንዲፈረጁ መንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡…፡ ትህነግ እና ኦነግ ሸኔ ባለፉት አመታት እየተናበቡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በጉራፈርዳ፤ በምዕራብ ወለጋ፤ በቤኒሻንጉል፤ በሱማሌ፤ በደቡብ ክልል እና በተለያዩ አካባዎች አንድ ጊዜ በማንነት ሌላ ጊዜ በሃይማኖት የሽብር ስራዎችን ሲፈጽሙ መቆየታቸውን የተናገሩት የጎንደር ነዋሪዎች ይህን ማስረጃ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ በማየት በሽብርተኝነት በመፈረጅ የቡድኑን ስም መጠሪያ መጠቀም እንዳይቻል መደረግ አለበት ነው ያሉት፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ምሁሩ ረዳት ፕሮፌሰር አበበ አሰፋ ህወሀት መንግስት በነበረበት ጊዜ መንግስታዊ ሽብር ይፈጽም እንደነበረ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ እንደሚቻል አስገንዝበዋል። ህገወጡ ቡድን ከስልጣን ከተባረረ በኋላም እጁን ሰዶ የሚፈጽማቸውና በተልዕኮ የሚያስፈጽማቸው ወንጀሎች እንደነበሩ ገልጸዋል፤ ይህም የሽብር ስራ እንደሆነ ነው የህግ ምሁሩ የተናገሩት፡፡ ከፈጸሙት የጥቃትና የዘር ማጥፋት ድርጊት አኳያ ሲታይ በአለማቀፉ ማህበረሰብ የሽብር ድንጋጌ ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ ቢያንስ እንጅ አይበዛም፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል ነው ያሉት የህግ ምሁሩ፡፡ ከሽብርተኝነት አዋጁ አንጻር ያገባኛል የሚሉ ድርጅቶች፤ አለማቀፉ ማህበረሰብ፣ ምሁራን እና መንግስት በጋራ ተቀናጅተው በመረጃ ቡድኖቹን በአለም አቀፍም ይሁን በሀገር ውስጥ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰሩ፡፡ ዘጋባው የአብመድ ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply