ህገወጥ የሚባልና ለሌላ ዓላማ ሊውል የነበረ የጦር መሳሪያ በባንካችን አልተገኘብንም ተባለ።        አሻራ ሚዲያ     ህዳር 04 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር የፋይናንስ…

ህገወጥ የሚባልና ለሌላ ዓላማ ሊውል የነበረ የጦር መሳሪያ በባንካችን አልተገኘብንም ተባለ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 04 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር የፋይናንስ…

ህገወጥ የሚባልና ለሌላ ዓላማ ሊውል የነበረ የጦር መሳሪያ በባንካችን አልተገኘብንም ተባለ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 04 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ የተገኘ የጦር መሳሪያ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በወጋገን ባንክ ውስጥ ተከማችተው ተገኙ የተባሉት የጦር መሳሪያዎች ህጋዊ እና ከፌደራል ፖሊስ በህጋዊ ሰነድ የተገዙ እና ለቅርንጫፍ ማስፋፋት ጥበቃ አገልግሎት የሚውሉ ናቸው ሲሉ የወጋገን ባንክ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ክንዴ አበበ ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ አለመሆናቸውን ምክትል ስራ አስፈጻሚው ነግረዋል። በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት የሚውል የጦር መሳሪያ በአዲስ አበባ ኮሚሽን ፍተሻ መገኘቱን ገልጸው የተገኘው የጦር መሳሪያ ከሚያስፈልገው ውጭ እንዳልሆነ የነገሩን ስራ አስፈጻሚው የተገኙት መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ በህጋዊ ሰነድ ከፌደራል ፖሊስ የተገዙ ስለመሆናቸው ገልጸውልናል፡፡ አቶ ክንዴ ጨምረውም በዚህ ሰዓት ሚዲያዎችና ማህበረሰቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply