ህገወጥ ግጦሽ  መስፋፋት ለአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተባለ

ህገወጥ ግጦሽ  በፓርኩ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ መሆኑንና ጫና እያሳደረ መሆኑን የአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ አስታውቋል።

በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ የዱር እንስሳት   የሚከናወነው ጥበቃ ተጠናክሮ   ቢቀጥልም  በፓርኩ ዙሪያ ባሉ አርብቶ አደሮች  የሚከወን ህገወጥ ግጦሽ ግን በከፍተኛ ሁኔታ  እየጨመረ መምጣቱን የአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ሃላፊ አደም መሀመድ ተናግረዋል፡፡
 
ህገወጥ አደን በፓርኩ ባይስተዋልም በከፍተኛ ሁኔታ ህገወጥ ግጦሽ እና አልፎ አልፎ ህገወጥ ሰፈራ  ግን እንደሚከናወኑ ገጸዋል።

የሚስተዋሉ ድርጊቶችን ለመቅረፍ በፓርኩ ጽፈት ቤት ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ሃላፊው  ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ 215 ኪሎ ሜትር  በምሰራቁ ክፍል የሚገኝ  አዋሽ ፓርክ ውስት ከ350 በላይ ዝርያ  ያላቸው አእዋፋት፣ ዱር እንስሳት ይገኙበታልም ተብሏል።

እሊኒ ግዛቸው
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply