ህገ ወጡ የህወሀት ቡድን በእጅ አዙር በሀገሪቱ ሲፈጽመው የነበረውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ በማይካድራ በሚኖሩ አማራዎች ላይ በመድገም የተደበቀውን ግብሩን አሳይቷል ተባለ፡፡…

ህገ ወጡ የህወሀት ቡድን በእጅ አዙር በሀገሪቱ ሲፈጽመው የነበረውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ በማይካድራ በሚኖሩ አማራዎች ላይ በመድገም የተደበቀውን ግብሩን አሳይቷል ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-04/03/2013/ ባህር ዳር ህገ ወጡ የህውሀት ቡድን በእጅ አዙር በሀገሪቱ ሲፈጽመው የነበረውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ በማይካድራ በሚኖሩ በንጹሃን አማራዎች ላይ በመድገም የተደበቀውን ግብሩን እንዳሳየ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ድርጊቱ ከኢትዮጵያውያን እሴት ያፈነገጠ ጭካኔ የተሞላበት ደርጊት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ህገወጡ ቡድን በማይካድራ የፈጸመው ጭካኔ ከሰባዊነት ያፈነገጠ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ሁሉም የህገ ወጡን የህወሀት ቡድን ሴራ እና ተንኮል ባለፉት አመታት የሚያውቀው በመሆኑ ከዚህ በላይ ጉዳት እንዳይደርስ በንቃት አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡ ቡድኑ አሁንም በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የአማራ ተወላጆችን የመጨፍጨፍ ስራ ሊሰራ ስለሚችል መንግስት አስቸኳይ እርምጃ ሊወስድበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ህገ ወጡን ቡድን ወደ ህግ ለማቅረብ በሚወስደው እርምጃ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡ ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply