ህግ የተላለፍ የሽያጭ መመዝገቢያ ተጠቃሚ ድርጅቶች ተቀጡ።88ሺህ 533 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በሚጠቀሙ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ 4,ሺ578 የሚሆኑት ህግ በመተላለፋቸዉ…

ህግ የተላለፍ የሽያጭ መመዝገቢያ ተጠቃሚ ድርጅቶች ተቀጡ።

88ሺህ 533 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በሚጠቀሙ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ 4,ሺ578 የሚሆኑት ህግ በመተላለፋቸዉ የቅጣት ዉሳኔ እንደተላለፈባቸዉ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር በድርጅቶቹ ላይ 1ሚሊዮን 254ሺህ 750 ብር ቅጣት እንዳስተላለፈባቸዉ ገልጿል ።

ይህ የተገለፀዉ የገቢዎች ሚኒስቴር የ2014/15 በጀት ዓመት ላይ በመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ ጥያቄን መሠረት በማድረግ ነዉ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 285ሺህ በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ እንደሚገኝ ቢገመትም በመሳሪያዎቹ ላይ በቂ መረጃ የማግኘት ከፍተኛ ችግር አለ ብለዋል።

በቅርቡ እያለሙት ባለዉ ቴክኖሎጂ አዲስ የሚያስገቧቸዉ የሽያጭ መመዝገቢያዎች GPS የሚገጠምላቸዉ መሆናቸዉንም ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂዉ በልፅጎ ወደ ስራ ሲገባ በአካል የሚደረግ የሽያጭ መመዝገቢያ ቁጥጥርም እንደሚቀነስ ለቋሚ ኮሚቴዉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ የታክስ አዋጅን ተላለፈዉ በተገኙ 1,818 መስሪያ ቤቶች ላይ የቅጣት ዉሳኔ እንደተላለፈባቸው አስታውቋል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ በበኩላቸው ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎችን በቴክኖሎጂ አዘምኖ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት ፈጥሮ ቢሠራ የታክስ ማጭበርበርንና ሐሰተኛ ደረሰኝን መከላከል ስለሚችል የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የሚረዳው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ከዛም ባለፈ የሽያጭ መመዝገቢያ የማይጠቀሙ በማንዋል እየተጠቀሙ ያሉ ግብር ከፋዮች አስገዳጅ በሆነ መነገድ ወደ ሲስተም እንዲመጡ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ተዳለ በእስር ላይ በመሆናቸዉ በምክትላቸዉ ስብሰባዉ ተመርቷል።

አቤል ደጀኔ

ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply