ህፃን ሳሙኤል ዩሃንስ በመጥለፍ ቤተሰቦቹን10 ሚሊዮን ብር ሲጠይቁ ነበር በተባሉ 3 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ!ተከሳሾቹ መሪጌታ ሚስጥሩ ይግዛው፣ ዘውዲቱ ገብሬ እና ብሩክ ቸኮል…

ህፃን ሳሙኤል ዩሃንስ በመጥለፍ ቤተሰቦቹን10 ሚሊዮን ብር ሲጠይቁ ነበር በተባሉ 3 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ!

ተከሳሾቹ መሪጌታ ሚስጥሩ ይግዛው፣ ዘውዲቱ ገብሬ እና ብሩክ ቸኮል ይባላሉ።

ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህጻን ልጅን በመጥለፍ ወንጀል ነው የተከሰሱት።

ክሱን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ከጠበቃ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡ ለህዳር 20 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

የዓቃቢህግ ክስ እንደሚያመላክተው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘውዲቱ ገብሬ ቀደም ብላ በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ስትሰራበት በነበረበት ቤት ውስጥ እድሜው 2 ዓመት ከ11 ወር የሆነው ህጻን መኖሩን ለአንደኛ ተከሳሽ መጠቆሟ ተጠቅሷል።

በዚህ መሰረት ከህጻኑ ቤተሰቦች ብር ለመቀበል በመነጋገርና በመስማማት 2ኛ ተከሳሽ ስራዋን ለቃ ከቆየችበት የመኖሪያ ቤት በድጋሚ ተቀጥራ እንድትገባ መደረጉ በክሱ ተዘርዝሯል፡፡

በስምምነታቸው መሰረት ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ክልል ልዩ ቦታው አያት ጣዕም ዳቦ ቤት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት የመኖሪያ ቤት ውስጥ ህጻን ሳሙኤልን ማስቲካ ልግዛለት ብላ በማታለል ይዛው ከቤት በመውጣት በወቅቱ እዛው አካባቢ ይጠብቁዋት ከነበሩ 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ጋር በመገናኘት ከአዲስ አበባ ውጭ ህጻኑን ጠልፈው መሰወራቸው በክሱ ተመላክቷል።

በዚህ መልኩ ከተሰወሩ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ ለህጻኑ አባት ስልክ በመደወል ህጻኑ ከእነሱ ጋር እንዳለ እና 10 ሚሊዮን ብር ካላመጡ እንደሚሸጡት በመግለጽና በማስፈራራት ሲደራደሩ እንደነበር በክሱ የተገለጸ ሲሆን በአ/አ ፖሊስ ÷በፌዴራል ፖሊስ እና በአማራ ክልል ፖሊስ እንዲሁም በደህንነት መስርያ ቤት ከፍተኛ ኦፕሬሽን ስራ በጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም 1ኛ ተከሳሽ በምስራቅ ጎጃም ዞን በአዲስ አለም ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መያዙ የተጠቀሰ ሲሆን

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ኢጅሬ ወረዳ አዲስ አለም ከተማ ጨረቃ ሠፈር በሚገኝው 1ኛ ተከሳሽ ተከራይቶት በነበረው ቤት ውስጥ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸው በክሱ ተገልጿል።ክሱን የተመለከተው ችሎት ተከሳሾቹ ከጠበቃ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡ ለህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply