ሆሊውድ ዩክሬንንና ዜሌኒስኪን በክብር አስቧልScreen Actors' Guild Awards ወይም ሳግ በተሰኘው የሽልማት ስነ ስርአት የሆሊውድ ተዋንያን ዩክሬንና መሪዋን በክብር አስበዋል፡፡የዩ…

ሆሊውድ ዩክሬንንና ዜሌኒስኪን በክብር አስቧል

Screen Actors’ Guild Awards ወይም ሳግ በተሰኘው የሽልማት ስነ ስርአት የሆሊውድ ተዋንያን ዩክሬንና መሪዋን በክብር አስበዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ መዝናኛው መስክ ያፈራቸው እንደሆኑም ተነስቷል፡፡

ብሪያን ኮክስ ሽልማቱን ሲቀበል ፤ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ኮሜዲያን እንደነበሩ ተናግሯል፡፡ ከፕሬዝዳንት ዜሌኒስኪ የመጀመርያው የምናከብርላቸው ነገር ምርጥ ኮሜዲያን መሆናቸውን ነው ያለው ብሪያን ኮክስ ከዚያ ደግሞ ወደ ፕሬዝዳንትነቱ መምጣታቸው ሌላው አስገራሚው ብቃታቸው ነው ብሏል፡፡

ሌላዋ ተወናይት ጄሲካ ቻስቴን ደግሞ ልቤ ለነፃነታቸውና ለደህንነታቸው እየተጋደሉ ካሉት ዩክሬናውያን ጋር ነው ብላለች፡፡

የቴሌቪዥን ሆስቷ ግሬታ ሊ ደግሞ በቀይ ምንጣፍ ላይ ስትንቀሳቀስ ሰማያዊና ቢጫ ቀለም ያለውን ልብስ አድርጋ ነበር፤ ሰማያዊና ቢጫ ቀለም የዩክሬን ባንዲራ ነው፡፡

ዜሌኒስኪ ከተዋናይነት እንደ አውሮፓውያኑ በ 2019 ፕሬዝዳንት እስኪሆኑ ያለው ጉዞ Servant of the People በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ የተንፀባረቀ ሲሆን ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚጥር መምህር ገፀባህሪ ተላብሰው ተጫውተዋል፡፡

ዜሌኒስኬ ሀገሩ በተወረረችበት በዚህ ወቅት ያሳዩት የተረጋጋ አመራር በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ አድናቆት እያገኘ ነው፡፡

ይሄ የኢንተርኔት እውቅና ከፍ ባለበት በዚህ ወቅት የድሮ ትወናዎቻቸው እየወጡ ሲሆን በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ያቀረቡት ዳንስም ትዊተር ላይ ተለቆ ማህበራዊ ሚዲያው እየተቀባበለው ነው፡፡

ብሪታኒያዊው ተወናይ ሀግ ቦንቪሌ በብሪታኒያ ታዋቂ የአሻንጉሊት ፊልም የሆነው Paddington Bear የዩክሬንኛውን ትርጉም በድምፅ ፕሬዝዳንት ዜሌኒስኪ እንደተጫወቱት አንስቶ በትዊተር ገፁ ለቆታል፡፡
ቢቢሲ

ሔኖከ አስራት
የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply