You are currently viewing ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል  – BBC News አማርኛ

ሆስፒታሎቿ በቁስለኞች እና በአስከሬን በተጨናነቁባት ጋዛ የአየር ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/dcb7/live/0645a8b0-7168-11ee-a503-4588075e3427.jpg

ማስጠንቀቂያ፡ በዚህ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሊረብሹ የሚችሉ መረጃዎች ተካተውበታል
በማዕከላዊ ጋዛ የሚገኘው አል-አቅሳ ሰማዕታት ሆስፒታል የአስከሬን መሸፈኛ እያለቀበት ነው።
አስከሬኖች ግቢ ውስጥ ተከማችተዋል። ጸሎት ሲካሄድና ዘመድ አዝማድ በሐዘን ብዛት ራሳቸውን ሲስቱ ይታያል።
የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች የቆሰሉትን ለማከም እና በጣም የተጎዱትን ለማዳን ደፋ ቀና ይላሉ። የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁስ ቀን ከቀን ወደ ቀን እየተመናመነ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply