ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል-  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው።

አቶ ገዱ የህግ የበላይነት ዘመቻ ድልን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክትም ኢትዮጵያዊነት አሸንፏል ብለዋል።

ክብርና ሞገስ ለመከላከያ ሰራዊትና ለአገራቸው ክብር ሲሉ ውድ ህይዎታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ሲሉም አመስግነዋል።

የአማራ፣ የአፋርና የሌሎችም ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ አባላት የእኛ መኩሪያዎቾ ናችሁና እጅ እንነሳለን ብለዋል።

ለህዝብና ለአገር ክብር የተሰው ጀግኖቻችን ዘላለማዊ ክብር ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

The post ለሀገር ክብር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በመስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ምስጋና ይገባል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply