You are currently viewing ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ እስር የቆዬው አሌክስ ሸገር ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ…

ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ እስር የቆዬው አሌክስ ሸገር ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ…

ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ እስር የቆዬው አሌክስ ሸገር ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ለሁለት ሳምንታት ያህል በግፍ እስር የቆዬው እና ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ከሄደ በኋላ በ5 ሽህ ብር ዋስትና መጋቢት 14/2015 የተፈታው አሌክስ ሸገር ድምጽ ለሆኑት ምስጋና አቅርቧል። አሌክስ ሸገር የደረሰበትን በደል በሚከተለው መልኩ ገልጾታል:_ “ወዳጅ ጓደኞቼ እህት ወንድሞቼ ያለ አንዳች ጥፋት ከ14 ቀን እስር በኋላ ሠበር ሠሚ ችሎት ድረስ ቀርቤ በ5 ሽህ ብር ዋስ መፈታቴን በፔጄ ላይ ለእናንተ እንዳልገልፅ ለሁለተኛ ጊዜ የእጅ ስልኬን የአዲስ አበባ ፖሊስ እስካሁን ድረስ ስለቀማኝ ከይቅርታ ጋር ማሳወቅ አልቻልኩም” ብሎታል። “በዚህም ምክንያት ከእናንተም ጋር ሆነ ሌላ ሀገር ካሉ ቤተሠቦቼ ጋር ጭምር መገኛኘት አልቻልኩም ነበር” ሲል ገልጧል። አሌክስ ሸገር በአገዛዙ በተደጋጋሚ ለግፍ እስር እየተዳረጉ ከሚገኙት የአዲስ አበባ ልጆች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply