ለሃገር ጥቅም ሲባል መሄድ የማንፈልግባቸው ቦታዎችም ላይም ቢሆን እንሄዳለን፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድጠቅላይ ሚንስትሩ ሰላምንና ብልፅናን ለማስቀጠል ስንል ጦርነትን ለማስቆም ተገደ…

ለሃገር ጥቅም ሲባል መሄድ የማንፈልግባቸው ቦታዎችም ላይም ቢሆን እንሄዳለን፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰላምንና ብልፅናን ለማስቀጠል ስንል ጦርነትን ለማስቆም ተገደናል ብለዋል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽ፡፡

ለሰላማችን ስንል ጦርነት ማቆምን መርጠናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ ጦርነት ሁሌም መጥፎ ነገር ነው፣ ነገር ግን ሁሌም ሰላም ጥሩ ነገር ነው ሲሉ የጦርነቱ መቋጫ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ገልፀውታል፡፡

ነገር ግን የኢትዮጵያ ህልውናም ሆነ የኢትዮጵያን ልእልና የሚፈታተን ነገር ሲፈጠር ለማስጠበቅ የሚደረገው እርምጃ አይታይም ብለዋል፡፡

ድርድርም ሆነ ውይይት የሚኖረው ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሃገር ጥቅም ሲባል መሄድ የማንፈልግባው ቦታዎችም ላይ ቢሆን እንሄዳለን፡፡

ሰላም የሚያስከፋቸው ሃይሎች የጦርነት ነጋዴዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡

ህግና ሰርዓት በሃራችን እንዲከበር የሚደረግ ማንኛውም ንግግርና ውይይት አይጎዳም ብለዋል በንግግራቸው፡፡

በየዉልሰው ገዝሙ

ህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply