ለህዝቡ የሚቀርበው የእንስሳት ተዋጽኦዎ የአለም የጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠዉ መመዘኛ በታች ነው ተባለ::በግብርና ሚኒሰቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ እንደ ስጋ፤ እንቁላል፤ ወተት…

ለህዝቡ የሚቀርበው የእንስሳት ተዋጽኦዎ የአለም የጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠዉ መመዘኛ በታች ነው ተባለ::

በግብርና ሚኒሰቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ እንደ ስጋ፤ እንቁላል፤ ወተት፤አሳ፤ ያሉ የእንስሳት ተዋፅዖዎች ፤ የአለም የጤና ድርጅት ዜጎች ማግኘት አለባቸዉ ብሎ ካስቀመጠዉ መስፈርት ልክ እያገኙ አይደለም ነዉ ያለዉ ፡፡

በግብርና ሚኒሰቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የሚኒሲቴረ ዴታዉ አማካሪ ዶክተር ዮሃንስ ግርማ የአለም የጤና ደርጅት አንድ ሰዉ በአመት 2 ማቶ ሊትር ወተት መጠጣት እንዳለበት ቢያስቀምጥም አሁን ላይ በሃገራችን ዜጎች እያገኙ ያሉት ከ 60 እስከ 70 ሊትር ያልበለጠ ነዉ ብለዋል ፡፡

ድርጅቱ ካስቀመጠዉ ደረጃ ጋር ለመድርስ አሁን ላይ በሃገራች የሚመረተዉን የወተት መጠን በሶስት እጥፍ ማሳደግ ይኖርብናል ነው ያሉት ፡፡

በአመት 8 ቢሊየን ሊትር ወተት እንደሚመረትና የነፍስ ወከፍ ፍጆታችን ላሟሟለት ወደ 22 ቢሊዮን ሊትር ወተት ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡
በዶሮ ስጋና እንቁላል ዘርፍም አንድ ሰዉ ማግኘት ከነበረበት የሚያገኘዉ እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ ብለዋል፡፡

ገበያ ተኮር የሆነ ስርዓት ያለመኖር፤የመኖ እጥረት ፤የእንስሳት የጤና ክትትል ችግር፤ ያሉት እንሰሳት ዝርያ ያለማሻሻል፤ ምክንያት መሆኑን ነግረዉናል፡፡

በመሆኑ አሁን ላይ ዘርፉን ለማሻሻልና ከዘርፉ የሚገባን ያህል ለመጠቀም በመንግስት ደረጃ ፖሊሲ ተቀርፆ እየሰራንበት እንገኛለን ብለዉናል፡፡

#በልዑል ወልዴ
ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply