ለሆስፒታሎች የሚቀርበው የደም አቅርቦት ላይ እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ።

ለሆስፒታሎች የሚቀርበው የደም አቅርቦት ላይ እጥረት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ሆስፒታሎች ከሚፈልጉት የደም አቅርቦት አንጻር የሚፈለገውን ያህል የደም አቅርቦት ማሟላት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሃብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ለካንሰር ታማሚዎች የሚውለው የፕላትሌት የደም አይነት ለአምስት ቀናት ብቻ የሚቆይ በመሆኑ፣ ከሌሎች የደም አይነቶች በተለየ ሁኔታ ተደጋግሞ እጥረት እንደሚያጋጥም ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ በበጎነት የደም ልገሳ እንዲያደርግም ጥሪ አቀርበዋል።
በየአመቱ የደም ፍላጎት በ10 በመቶ እያደገ እንደሚገኝ የብሔራዊ የደም ባንክ ጠቁሟል።

በተለይም የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሕይወትን እንዲሁም የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችን እና በጽኑ ህመም ላይ የሚገኙ በሽተኞችን ሕይወት ለመታደግ የተፈጠረውን የደም እጥረት ለመፍታት የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅም ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply