ለሕክምና ባለሙያዎች ስፔሻሊቲ ስልጠና መስጠት የሚያስችል የብቃት ምዘና ፈተና እየተሰጠ ነው

ለሕክምና ባለሙያዎች ስፔሻሊቲ ስልጠና መስጠት የሚያስችል የብቃት ምዘና ፈተና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕክምና ባለሙያዎች ስፔሻሊቲ ሥልጠና መስጠት የሚያስችል የብቃት ምዘና በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው 4 ሺህ 800 ለሚሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪ የሕክምና ባለሙያዎች በ22 ማዕከላት እየተሰጠ መሆኑን በሚኒስቴሩ የሰው ሀብት ልማት ሜዲካል ትምህርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሐመድ ቴኒ ገልጸዋል።

ፈተናውን በብቃት የሚያልፉ 1 ሺህ ሐኪሞች በ22 የሕክምና የትምህርት መስኮች በ16 የሕክምና ተቋማት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የስፔሻሊቲ ስልጠናው የሰው ኃይል በሚፈለግባቸው የትምህርት መስኮች የሚሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ፕሮግራሙ የጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሻሻል ከሚተገብራቸው ፕሮግራሞች አንዱ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ለሕክምና ባለሙያዎች ስፔሻሊቲ ስልጠና መስጠት የሚያስችል የብቃት ምዘና ፈተና እየተሰጠ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply