ለመላው አማራና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከጥቃቅን ልዩነቶች ወጥተን ስለሀገርና ህዝብ አንድነት ሲባል አንድ ሆነንና ተረጋግተን እርስ በርሳችን የምንጠባበቅበትና የምንደጋገፍበት ጊዜ ላ…

ለመላው አማራና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከጥቃቅን ልዩነቶች ወጥተን ስለሀገርና ህዝብ አንድነት ሲባል አንድ ሆነንና ተረጋግተን እርስ በርሳችን የምንጠባበቅበትና የምንደጋገፍበት ጊዜ ላ…

ለመላው አማራና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከጥቃቅን ልዩነቶች ወጥተን ስለሀገርና ህዝብ አንድነት ሲባል አንድ ሆነንና ተረጋግተን እርስ በርሳችን የምንጠባበቅበትና የምንደጋገፍበት ጊዜ ላይ መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) ከተቋቋመበት አላማ አንጻር የአማራ ህዝብ፣የመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የሀገር ጉዳይ ያገባኛል ብሎ ከእነ ጫናው ቢሆን እየተንቀሳቀሰ መቆየቱና ለወደፊቱም በዚህ ማዕቀፍ ስር ሆኖ እንደሚንቀሳቀስ ተገልጧል። የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ በአማራ ህዝብ ላይ አነጣጥሮ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀልም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ተስፋ በቆረጡ እብሪተኛ ሀይሎች የሚፈፀመው ጥቃት፣አገርንና አብሮነትን ለማፍረስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በማውገዝ ሁሉም ነቅቶ ራሱን፣ጎረቤቱን፣አካባቢውን ብሎም ሀገሩን እንዲጠብቅ ሲል አሳስቧል። በመከላከያ ሰራዊት ላይ በህወሀት የተከፈተው ተኩስም የህወሀት እብሪትና ማንአለብኝነት ጫፍ መድረስንና ሀገር ለማፍረስ ያለውን አቋም በግልፅ ያሳየ ስለመሆኑም ተጠቁሟል። ጥቃቱ አብሮነትን፣ሉአላዊነትና ወንድማማችነትን የሚፈታተን በመሆኑ መላው የአማራ ህዝብ፣የአማራ ወጣቶች፣የአማራ ተማሪዎች፣ፋኖዎች፣ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የምሁራን መማክርት፣የፀጥታ መዋቅሩ፣ሲቪክና ሌሎች አደረጃጀቶች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ብሏል። በአሁኑ ሰዓት ራስን፣ወገንን፣ አካባቢን ብሎም ሀገርን ነቅቶ ከሰርጎ ገቦች እንቅስቃሴ መጠበቅ አስፈላጊ ነው ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። ህወሀት ትናንት ምሽት ላይ ጥቃት በከፈተባቸው ራያ፣በግዳን፣ በሰቆጣ፣በሁመራ፣ዳንሻ፣ጠገዴ ሶሮቃ፣በወልቃይትና በሌሎችም ያላችሁ ወገኖች አካባቢያችን ነቅተን በመጠበቅና የተደራጀ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል። መላው ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ከወሎ አማራ ህዝብ ጋር በታሪክም ሆነ በስነ ልቦና ተቀራራቢ ፍላጎት ያለው የአፋር ህዝብ እንዲሁም ወጣቶች ራሳችሁን ብሎም ሀገርን ለመጠበቅ እያደረጋችሁት ያለው እንቅስቃሴን ምንም እንኳ ይህ ተግባርና አቋማችሁ አዲስ ባይሆንም በአድናቆት እንመለከተዋለን፤ እናመሰግናለን ነው ያለው። አፋር አዋሳኝ በሆኑ አካባቢዎች የህወሀት ሰርጎ ገብ እንቅስቃሴዎች እንዳይኖሩና ካሉም ቀድሞ ለመከላከልና ለመመከት ዝግጁ መሆን አለበት ነው ያለው የአወማ ሊቀመበር ወጣት አስናቀ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply