You are currently viewing ለመላው የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን ለንቅናቄያችን ፬ኛ ዓመት የምስረታ ቀን አደረሰን፤ አደረሳችሁ! ***** አቶ ክርርሰቲያንታደለ እነሆ ዛሬ አብን ፬ ዓመት ሞላው። እንኳን…

ለመላው የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን ለንቅናቄያችን ፬ኛ ዓመት የምስረታ ቀን አደረሰን፤ አደረሳችሁ! ***** አቶ ክርርሰቲያንታደለ እነሆ ዛሬ አብን ፬ ዓመት ሞላው። እንኳን…

ለመላው የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን ለንቅናቄያችን ፬ኛ ዓመት የምስረታ ቀን አደረሰን፤ አደረሳችሁ! ***** አቶ ክርርሰቲያንታደለ እነሆ ዛሬ አብን ፬ ዓመት ሞላው። እንኳን አደረሰን፤ እንኳን አደረሳችሁ! አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ ንቅናቄያችን ባለፉት ፬ ዓመታት በርካታ ውጣውረዶችን በማለፍ ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋን የሚፈነጥቁ ጅምሮችን በማነሳሳትና በማነቃቃት፣ ወጣቶች የነገ ተስፋ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬ የአገር መሪና የሐሳብ ፊታውራሪ መሆናቸውን በማንበርና ከዚህ አንፃር የነበሩ በጎ ያልሆኑ ልማዶችን እንዲቀየሩ ፈር በመቅደድ፤ ታላላቆች ጉርምስና አስቸግሯቸው አገርን ለብትና በሚዳርጉ የርስ በርስ መቧቀስ ውስጥ ሲገቡ ሕዝብን በማረጋጋትና ለአገር አንድነት እንዲሁም ለወደፊት አብሮነት ትክ የለሽ ሚና የተጫወቱ የፖለቲካ አቋሞችን በመውሰድ፤ በምሑር ጠልነት የተተበተበውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሰረቱ በማረቅ እና ንቅናቄ በመፍጠር ምሁራን በአገራቸውና ሕዝባቸው ጉዳይ የመሐል ተጫዋቾች እንዲሆኑ በማስቻል፤ ዋልታ ረገጥ የፖለቲካ ትርክቶችን በእውነትና በእውቀት በመመከት ጠርዘኞች ወደ ፍትኃዊ አማካይ እንዲመጡ በመሞገት፤ ከ50 ዓመታት በላይ የተንጋደደውን የፖለቲካ ተረክ መንጋደድ ለማቃናት የሐሳብ አፍላቂነትና መሪነት ሚናን በመወጣት እንዲሁም በተመሰረተ በእጭር ጊዜ ውስጥ በምርጫ በመሳተፍ በአገራችን ባሉ የፌዴሬሽን፣ ክልልና የፌዴራል ምክርቤቶች መቀመጫዎችን በማሸነፍ በመቀመጫ ወንበርም እና በመራጭ ድምጽ ስሌት የኢትዮጵያ ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሆኑን በማረጋገጥ ጉልህ ስኬቶችን አስመዝግቧል። ከዚህ ጎን ለጎን የአባላት ግድያ፣ መታሰር እንዲሁም የትግል ጎራ መደበላለቅን የመሳሰሉ አሳዛኝና ንቅናቄያችንን የፈተኑ ጉዳዮችንም አሳልፈናል። በቀጣይ አብን እንዲወለድ ምክንያት የሆኑ የሕዝባችንን የኅልውና ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ፤ ወቅቱ ከሚጠይቀው አገራዊና ቀጠናዊ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዎች እውነታዎችና ፍላጎቶች የአገራችንና የሕዝባችንን ስትራቴጂካዊ መብቶች፣ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ባስከበረ መልኩ እንዲከወኑ ከበጎ ኃይሎች እና ከመላው ሕዝባችን ጋር በመሆን ለመታገል ከወትሮው የላቀ ንቃት፣ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና መደርጀት የሚያስፈልግ መሆኑን በማጤን መላው የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎቻችን የምስረታ በዓሉን ትዘክሩት ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። ፍትኅ፣ ነፃነትና እኩልነትን መለያ ቀለማት ያደረገውን ንቅናቄያችን አብን የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ አምበል ሆኖ እንዲወጣ በጎ ሚናችሁን ስትወጡ የነበራችሁ ሁሉ፤ ለእስካሁኑ ድጋፋችሁ ምስጋና እያቀረብሁ፤ በቀጣይም የተጠናከረ አለኝታነታችሁ እንዳይለየን አደራ ማለት እፈልጋለሁ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ! @አቶ ክርስቲያን ታደለ

Source: Link to the Post

Leave a Reply