ለመልሶ ግንባታ ከፍተኛ ችግር የገጠመዉ የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ድጋፍ ጠይቋል፡፡ለሁለት ዓመታት በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ድጋፍ…

ለመልሶ ግንባታ ከፍተኛ ችግር የገጠመዉ የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ድጋፍ ጠይቋል፡፡

ለሁለት ዓመታት በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ድጋፍ ይደረግልኝ ብሏል፡፡

ጥያቄዉ በቀጥታ ለፌደራሉ መንግስት የቀረበ ሲሆን ፤ ከጦርነቱ በፊት የባንክ ብድር ተፈቅዶላቸዉ የነበሩ ኢንቬስተሮች የሚገጥማቸዉን ችግር በመፍታት መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲል ነዉ ቢሮዉ የጠየቀዉ፡፡

የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሃላፊ መሃሪ ገ/ሚካኤል የመንግስት ጣልቃ ገብነት በእጅጉ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል፡፡

መንግስት የወለድ መጠንን በመቀነስ እና በዝቅተኛ የወለድ መጠን ደግሞ አዳዲስ ብድሮችን በመስጠት ለ3ዓመታት የተቋረጠዉን እና ብዙ ችግሮች ያሉበትን ይህን ዘርፍ መልሶ ማቋቋም ይኖርበታል ሲሉ ነዉ የገለጹት፡፡

ከፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት በኋላ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የትግራይን የኢንዱስትሪ ሴክተር መልሶ ለመገንባት ትብብር እንደሚያደርግ ገልጾ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድጋፍ ማድረግ አለመቻሉ የሚታወቅ ነዉ፡፡

ከጦርነቱ በፊት በትግራይ 61 ዋና የሚባሉ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ነበሩ፡፡ ከጦርነቱ በኋላ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ሙሉለሙሉ አልያም በከፊል ወድመዋል፡፡

እንደ መሰቦ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በድጋሚ መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ፤ሌሎች ጦርነቱ ባሳረፈባቸዉ ከባድ ጫና ምክንያት እስካሁን ምንም ዓይነት ስራ አለመጀመራቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply