ለመተከል ተፈናቃዮች የሁለተኛ ዙር እርዳታ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ተጀመረ          አሻራ ሚዲያ     ታህሳስ 30 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ከመተከል ሰባት ወረ…

ለመተከል ተፈናቃዮች የሁለተኛ ዙር እርዳታ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ተጀመረ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 30 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ከመተከል ሰባት ወረ…

ለመተከል ተፈናቃዮች የሁለተኛ ዙር እርዳታ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ተጀመረ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 30 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ከመተከል ሰባት ወረዳዎች ተፈናቅለው በርሀብ እና እርዛት ላይ ለሚገኙ አማራዎች በሚደረገው የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፉ የሚገኙትን እነ ምስጋናው በለጠ(ምስጋናው ዘ ግዮን) ፤ምናልባት ይታየው፤ጥላሁን አበጀን ከአሁን በፊት ባደረጉት ከፍተኛ የእርዳታ ማስተባበር ስራ አሁንም የእርዳታውን ሂደት እንዲያስተባብሩ የቻግኒ ወረዳ እና የመተከል ዞን አስተዳደር ድጋሜ ጠይቀዋል፡፡ እነርሱም የመተከል ዞን አስተዳደርና የቻግኒ ወረዳ በጠየቋቸው መሰረት እንዳለፈው ጊዜ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡ በዚህም በሁለተኛ ዙር የድጋፍ ማሰባሰብ መርሀ ግብሩ በመላው ዓለም የሚገኙ የአማራ ተወላጆችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ፈጥኖ ለመድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለመተከል ተፈናቃዮች እርዳታ ማድረግ የምትፈልጉ ካላችሁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000344972797 መጠቀም ትችላላችሁ ሲሉ እውቅና ያገኙት ግለሰቦች ተናግረዋል ። በመሆኑም በሁለተኛ ዙር የእርዳታ መሰባሰብ ዘመቻው የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ ዋና አስተባባሪዎችም፡- 1/ ዶክተር አያሌው አባተ (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ) 2/ አቶ በውቀቱ በላይ (ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ) 3/ አስር አለቃ መሀመድ ኑር(ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ) 4/ አቶ ወርቅነህ የኔው (ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ) 5/ አቶ ካሳሁን ታምሩ(ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ) ሲሆኑ እርዳታውን በማሰባሰብ ሂደት ውስጥ ሁሉም የበኩሉን መልካም ትብብር ያደርግ ዘንድ ተጠይቋል፡፡ ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply