ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በሚል ከቀበሌ ተመልምለን ወደ ነቀምት ከተወሰድን በኋላ በአማራዊ ማንነታችን ብቻ እንድንመለስ ተደርጓል ሲሉ በጉቶጊዳ ወረዳ የጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ወጣቶች ተናገሩ።…

ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በሚል ከቀበሌ ተመልምለን ወደ ነቀምት ከተወሰድን በኋላ በአማራዊ ማንነታችን ብቻ እንድንመለስ ተደርጓል ሲሉ በጉቶጊዳ ወረዳ የጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ወጣቶች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶጊዳ ወረዳ ከጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ለመከላከያ ሰራዊት በሚል ተመልምለው ወደ ነቀምት ከተወሰዱ በኋላ እንዲመለሱ ከተደረጉት ወጣቶች መካከል አንዱን እና ሌላ አንድ የአካባቢው ነዋሪን አነጋግሯል። የጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 11 ወጣቶች ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በሚል ከቀበሌ ተመልምለው የካቲት 29/2015 ወደ ነቀምት በጸጥታ አካላት ታጅበው ተወስደዋል። ከተወሰዱ እና የሜዲካል ምርመራውን ካለፉ በኋላ ግን በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ እንድንመለሱ ስለመደረጉ ገልጸዋል። ከቀበሌ ተመልምለው ወደ ነቀምት ከተወሰዱ በኋላ 2 ልጆች በሜዲካል ምርመራ እንዲመለሱ መደረጉ ተወስቷል። በ3ተኛ ቀናቸው እንዲመለሱ የተደረጉት ወጣቶችም:_ 1) አድምጠው ካሳሁን እና 2) ያብባል ይባላሉ። ለ10 ቀናት ያህል በወረዳ የስብሰባ አዳራሽ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ግን “እናንተ አታስፈልጉም” በሚል ከቀበሌው ተመልምለው የተላኩ አማራዎች ተለይተው እንዲመለሱ ስለመደረጉ ተገልጧል። በአጠቃላይ ከጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ለመከላከያ ሰራዊት በሚል ተመልምለው ከተላኩ እና ከተጉላሉ በኋላ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ወጣቶችም:_ 1) አድምጠው ካሳሁን፣ 2) ሰለሞን ባህሩ፣ 3) ማንደፍሮ ልዬው፣ 4) ማስረሻ፣ 5) ሸጋ ታዴ፣ 6) አየነው ቢያልፈው፣ 7) ልብሞኝ፣ 8 አቡሻ፣ 9) ካሳሁን ጎበዜ፣ 10) ሙሉቀን ዳኛቸው እና 11) ያብባል የሚባሉ ወጣቶች ናቸው። ከ100 በላይ የኦሮሞ ተወላጆችን ወደ ጉቶጊዳ ወረዳ ባቀኑ በ7ኛ ቀናቸው ለይተው ገንዘብ እየከፈሉ ለስልጠና ሲልኩ የአማራ ልጆችን ግን ያለምንም ክፍያ ከአስር ቀናት የአዳራሽ ቆይታ በኋላ ወደ ቀበሌያቸው እንዲመለሱ አድርገዋል በሚል ካድሪዎች ተወቅሰዋል። “እዚህ ተቀምጣችሁ ኦሮምኛ ለምን አትችሉም?” በሚል ጥያቄ ሁሉ በአንዳንድ የጉቶጊዳ ካድሪዎች ስለመጠየቃቸውም ምንጮች ተናግረዋል። በጉቶጊዳ ወረዳ ካድሪዎች ዘረኛ አሰራር የተነሳ በአማራዊ ማንነታችን ብቻ መጋቢት 21/2015 በ10ኛ ቀናችን ወደ ቀበሌያችን ታጅበን እንድንመለስ ተደርጓል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply