ለሥራ ቅጥር የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት መስፈርት መጠየቃቸው ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

ለሥራ ቅጥር የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት መስፈርት መጠየቃቸው ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለሥራ ቅጥር የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት መስፈርት መጠየቃቸው ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው የሕግ ባለሙያዎች ለሸገር ተናግረዋል፡፡ የሕግ ባለሙያዎቹ ያቀረቡት ምክንያት በሕገ መንግሥቱ የከተማዋ አስታደደር ሥራ ቋንቋ አማርኛ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ከአንድ የፓርላማ አባል ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሰኞ’ለት በጥያቄ መልክ ተነስቶላቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን፣ እንዲህ ዐይነት አሠራር ሊበረታታ ይገባዋል በማለት ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ሸገር ኤፍ ኤም እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply