ለሴቶች እና ድጋፍ ለሚሹ አካላት በመሬት ላይ መብት ይሰጣል የተባለለት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡አዋጁ ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ አባወራዎች…

ለሴቶች እና ድጋፍ ለሚሹ አካላት በመሬት ላይ መብት ይሰጣል የተባለለት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

አዋጁ ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ አባወራዎች ሚስቶች የገጠር መሬትን በፍትሃዊነት የይዞታ ባለቤት ያደረጋል የሚለው ሀሳብ ላይ በርካታ ጥያቄ እና አስተያየቶች ተሰጥተውበታል፡፡

የምክር ቤት በዛሬው ውሎ ከአባላቱ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ምላሽ ይሰጠን ሲሉ አፈ-ጉባኤውን አቆርጠው የነበረ ሲሆን በርካታ ጉምጉምታም በምክር ቤቱ ተሰምቷል፡፡
በዛሬው ዕለት የግብርና ጉዳዮች እና የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ያዳመጠው ምክር ቤቱ ረቁቅ አዋጁን በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ አድርጎታል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6 2016 ባደረገው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

አዋጁ ለሴቶችና ድጋፍ ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመሬት ላይ መብት የሚሰጥ፣ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ በመሬት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የአርብቶ አደሩን መብትና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ተቃኝቶ የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

አዋጁ ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ አባወራዎች ሚስቶች የገጠር መሬትን በፍትሃዊነት የይዞታ ባለቤት ለማድረግ ይረዳል ተብሏለታል፡፡
በዚህ ዙሪያ ላይ የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችንና ውይይቶችን አድርገውበታል፡፡

ይህንንም በተመለከተ አንድ የምክር ቤት አባል ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ አባወራዎችን በተመለከተ ሁለተኛ ሚስት ድርሻ ይኖራታል የሚለው ሀሳብ “ድርሻውን ማነው የሚወስነው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

“በዚህም ይህ አዋጅ አሁንም ከቤተሰብ ህጉ ጋር እንዳይጣረስ መጠንቀቅ አለብን ዛሬም ፍርድ ቤቶች በባል እና ሚስት መካከል ብዙ ክርክር ስላለ ይህም የክርክር መንስኤ እንዳይሆን” ሲሉ አፅንኦት ይሰጠው ብለዋል፡፡
ከዚህ ውጪም የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ለቋሚ ኮሚቴዎቹ አቅርበዋል፡፡

በዚህም የተጠቃሚነት መብትን ማስፋት፣ የከፊል አርብቶ አደርና አርብቶ አደሩን የመሬት አያያዝና አስተዳደር ያካተተ፣ የገጠር መሬት ምዝገባና ቅየሳ ሕጋዊ ማዕቀፍ የሰጠ መሆን ይገባዋልም ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀድም ጣብያችን በኢትዮጵያ 11 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ተጨማሪ ሚስቶች እንዳላቸው በምክር ቤቱ መነሳቱ ጠቅሷ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply