“ለስልጣንና ጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የአማራ ልዩ ሀይልን ስም ሲያጠፉና ከራያ አላማጣና ራያ ጨርጨር አካባቢዎች ወጥቶ እነሱ እንዳሻቸው እንዲፏልሉ በዚሁ መከረኛ ፌስቡክ ብቻ ሳይወሰኑ በሚፈጠሩ መድ…

“ለስልጣንና ጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የአማራ ልዩ ሀይልን ስም ሲያጠፉና ከራያ አላማጣና ራያ ጨርጨር አካባቢዎች ወጥቶ እነሱ እንዳሻቸው እንዲፏልሉ በዚሁ መከረኛ ፌስቡክ ብቻ ሳይወሰኑ በሚፈጠሩ መድረኮች ላይ ያለሀፍረት ሲጠይቁ ይስተዋላሉ።” ዶ/ር ሲሳይ መምግስቴ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መ/ር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መ/ር የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ወደ ሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ፣ ራያ አላማጣና ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማቅናት ትዝብታቸውን በይፋዊ የፌስ ቡክ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከልም ወደ ራያ ቆቦና አላማጣ ባቀናበት ወቅት ከታዘበው መካከል እንዲሁም ታህሳስ 25 ቀን 2013 ቆቦ ላይ በነበረው የራያ ህዝብ የምክክር መድረክ ላይ በስፋት የተነሳውም የአማራ ልዩ ሀይልን ስም በማጠልሸት ከአካባቢው እንዲወጣና እንደፈለጉ ለመሆን የሚፈልጉ አካላትን እንዳሉና እነዚህኞችን ጁንታዎች መንግስት ያስቁምልን የሚለው ይገኝበታል። በመድረኩ ላይ እድሜ ለአማራ ልዩ ሀይል፣ለፋኖ፣ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት ዕድሜ ለግፍ ጠሉ ለራያ ህዝብ በማለት ምስጋናቸውን ያቀረቡት በርካቶች ናቸው። የአማራ ልዩ ሀይል በራያ ግራካሶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ውድ ህይወቱን በመገበር ነጻ እንድንወጣ ያደረገ ጀግና ነው ሊመሰገን ይገባዋል ሲሉ ተደምጠዋል። የዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ትዝብት የሚከተለው ነው:_ ከላሽንኮቭ በዚህ መልክ መያዝ አቁሜ በምትኩ ብዕርና ጠመኔ/ማርከር መጨበጥ ከጀመርሁ ከሀያ አምስት አመታት በላይ ተቆጠርዋል። ዛሬ ግን ጀግኖቹን የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ስመለከት ትውስታየን ቀሰቀሱትና ለደቂቃዎችም ቢሆን ይህን ክላሽ እንዲዚህ ይዤ ፎቶ ተነሳሁበት። የአማራ ልዩ ሀይል አባላትንና ሚሊሻን ጀግንነት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ጀነራል መኮንኖች በሚገርም ሁኔታ ነው የሚገልጹት። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከተራ ወታደር እስከ የራያ ግንባርን ከመሩ ጀነራሎች ጋር የመገናኘት ዕድል ተፈጥሮልኝ ነበር። እናም የሰራዊቱ አባላትና አመራሮቹ ስለአማራ ልዩ ሀይል ጀግንነትና አገር ወዳድነት አውርተው አይጠግቡም። በዛ ላይ የአማራ ክልል ህዝብ በአጠቃላይና የሰሜን ወሎ ህዝብ ደግሞ በተለይ በራያ ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት የሰጠውን ሁለገብ ድጋፍና እንክብካቤ ሲገልጹማ ሲቃ እየተናነቃቸው ነው። በጥቅሉ በሁሉም መስኩ ከጎናችን ስለነበሩ ቁስለኞችን ሲንከባከቡና በጦር ግንባር ሲዋጋ የነበረውን ሰራዊት በአካል እየተገኘ ሲያበረታቱ ነበረ ብለዋል። እውነታው ይኸ ሆኖ ሳለ የእኛዎቹ ማፈሪያዎች ለስልጣንና ጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የአማራ ልዩ ሀይልን ስም ሲያጠፉና ከራያ አላማጣና ራያ ጨርጨር አካባቢዎች ወጥቶ እነሱ እንዳሻቸው እንዲፏልሉ በዚሁ መከረኛ ፌስቡክ ብቻ ሳይወሰኑ በሚፈጠሩ መድረኮች ላይ ያለሀፍረት ሲጠይቁ ይስተዋላሉ። ከዛም አልፈው የልዩ ሀይሉ አብሮት ከተዋደቀው የመከላከያ ሰራዊት ጋር እንዲገጭ ለማድረግ ይጥራሉ። ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ በጀግንነት ነጻ ያወጣው የራያ ህዝብ ግን በተቃራኒው የአማራ ልዩ ሀይልማ የትም አይሄድም ሲል ቁርጣቸውን ነግሯቸዋል። እናም እኛም አባቶቻችን በኩራት ሲሉት እንደነበረው ሁሉ: በለው በመዋጣ ድገመው በዋንዛ፣ በአባት ርስትና በሚስት የለም ዋዛ። በማለት የአማራ ልዩ ሀይልና ፖሊስ ነጻ ያወጣውን ወገኑን እና ርስቱን ትቶ ሊወጣ እንደማይችል፣ እንዳውም ሀይሉን ይበልጥ አጠናክሮ መከላከያን ሊተካ እንደሚችል ቁርጡን በመንገር ሲያምራችሁ ይቅር ብለናቸዋል። እነሱስ ሞኝ ሆነው ነው እንጂ ለ30 አመታት ታፍኖ የነበረን ህዝብ በትግላቸው የነጻነት አየር እንዲተነፍስ ካደረጉ በኋላ እንዴት ይተውታል። በነገራችን ላይ የቆቦ ከተማና አካባቢው ህዝብ በጦርነቱ የተሰው ወታደሮችን ልክ የቅርብ ቤተሰብ አባል የሞተበትን ያህል ከልቡ እያነባ በስርአቱ የቀበረ ሲሆን ክርስቲያኖችን ተስካራቸውን ሙስሊሞችን ደግሞ ሰደቃቸውን ለማውጣት ገንዘብና እህል በማዋጣት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply