ለስደተኞች የሚረዳ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ለስደተኞች የሚረዳ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁለገብ መረጃ የሚያቀርብ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡

በዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት ተዘጋጅቶ ይፋ የተደረገው መተግበሪያ ለስደተኞች የተሟላ መረጃ መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ስደተኞች መረጃ ባለማግኘታቸው ምክንያት ለእንግልት እንደሚዳረገው ድርጅቱ በዚህ ወቅት ገልጿል፡፡

አዲሱ የሞባይል መተግበሪያ ግን ከስደት ሕይወት ጋር በተገናኘ የሥራ ዕድል አማራጮችን፣ የየሃገራት ህግጋትንና የሚደርሱ ችግሮችን በዘርፉ ከሚሰሩ ተቋማት እና ኤምባሲዎች ጋር በማስተሳሰር መረጃዎችን በማቅረብ ለስደተኞች እገዛ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

መተግበሪያው በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እዲሰጥ ተደርጎ ነው የተዘጋጀው፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዔታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ የሞባይል መተግበሪያው ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ለስደተኞች የሚረዳ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply