ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅታቸው እስከምን ድረስ ነው

ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዝሞ በ2013 ዓ.ም እደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በዚህ መሰረት የምርጫው ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሆነ ቦርዱ የገለጸ ሲሆን የምርጫ ውጤትም በቦርዱ ይፋ የሚደረገው ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚሆን ተገልፃል፡፡

አሐዱም ከፖለቲካ ፓርቲነት ከመሰረዝ የተረፉና በምርጫው ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጊዜ ሰሌዳውን እንዴት ተመልክተውታል? ፓርቲዎቹ ያላቸው አቋምና ዝግጁነትስ አስከምን ድረስ ነው? እንዲሁም ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ከስጋት የጸዳ ምርጫ ለማካሄድ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ምን አስበዋል? የሚለውን በዕለቱ አጀንዳ ሊመለከተው ወዷል፡፡

አዘጋጅ እና አቅራቢ፡ ፀጋነሽ ደረጀ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply