ለስድስት ወራት የተፋለሙ የዋግ ሚሊሻዎች ጀግንነት! የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 26 2014 አ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ዋግ በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ኹነቶች የተከናወኑበት አካባቢ ነው።…

ለስድስት ወራት የተፋለሙ የዋግ ሚሊሻዎች ጀግንነት! የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 26 2014 አ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ዋግ በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ኹነቶች የተከናወኑበት አካባቢ ነው። ዋግሹሞችን አንግሳለች። ከውጭ ጠላት ጋር ተናንቀው ለሀገራቸው የተዋደቁ እንደ ደጅ አዝማች ኀይሉ ከበደ የመሰሉ ጀግኖችንም አፍርታለች። ሰንሰለታማ ተራሮቿ እና ሸለቆዎቿ ለጀግኖቿ ኀይልና ብርታትን በመስተት ጠላት መውጫ መግቢያ እንዲያጣ አድርገዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በፈጸመ ጊዜም እነዚህን ሰንሰለታማ ተራሮች እና ሸለቆዎች እንደ ደጀን በመጠቀም የአኹኖቹ ጀግኖች መውጫና መግቢያ በማሳጣት የአባቶቻቸውን ጀግንነት ደግመውታል። ለዚህ ደግሞ የጻግብጅ ወረዳ ሚሊሻዎች ምሳሌዎች ናቸው። የጻግብጅ ወረዳ የትግራይ ክልል አዋሳኝ እንደመኾኑ ከዚህ በፊትም የሽብር ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በአካባቢው ላይ ግፍና በደል ሲፈጽም መቆየቱን የሚሊሻ አባላቱ ነግረውናል፤ አኹን ላይም በሽብር ቡድኑ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ ኾኗል። የሽብር ቡድኑ በወረዳው ወረራ በፈጸመበት ወቅት ንጹሃንን ገድሏል፤ የመንግሥት እና የግለሰብ ሃብት እና ንብረት በመዝረፍ እና በማውደም ለሕዝብ ያለውን ጥላቻ በገሃድ ማሳየቱን ነው የነገሩን። የሽብር ቡድኑን ካርበደበዱት የሚሊሻ አባላት መካከል ምሩጽ ገብረ መድህን አንዱ ናቸው። አቶ ምሩጽ እንደነገሩን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሰቆጣን እና ድሃናን አልፎ በተቆጣጠረበት ወቅት የጻግብጅ ወረዳ ሚሊሻ ዝም አላለም፤ ነፍጡን አንስቶ ዱር ቤቴ አለ እንጂ። በሽብር ቡድኑ ላይ በፊት ለፊት እና በደፈጣ በተሰነዘረበት ጥቃት ከባድ ኪሳራ ደርሶበታል። የሽብር ቡድኑን የተፋለመው የሚሊሻ አባሉ ብቻ አልነበረም። ባለፉት 30 ዓመታት በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን የጎጠኝነት አገዛዝ የተንገፈገፈው ሕዝብ ዳግም በባርነት አገዛዝ ላለመውደቅ ከአዋቂ እስከ አዛውንት ድረስ ለወገን መረጃ በመስጠት እና ምግብ በማቅረብ፣ ለጠላት ደግሞ መረጃ በማሳሳት እና ምግብ በመከልከል ጭምር ታግሏል። አዲሱ ብርሃኑ እንደነገረን ደግሞ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዞኑን ለመውረር በመዘጋጀት ላይ እንዳለ የወረዳው ሚሊሻ ከአካባቢው ሕዝብ ጋር ጠላትን ለመመከት በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ ውይይት አድርጓል። ባለፉት ዓመታት ተጽዕኖ ሲደርስበት የቆየው ሕዝብም ዋግን ዳግም ላለማስደፈር ኹሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ የጋራ ውሳኔ ላይ ተደረሰ፤ ሚሊሻው በነፍጡ ለመፋለም፣ ነዋሪው ደግሞ ለወገን መረጃ በመስጠት እና ስንቅ በማቅረብ። ቀድሞ የሥነ ልቦና ትጥቅ የታጠቁት የሚሊሻ አባላት በደረሱት ስምምነት መሠረት ስንቁን ከደጀኑ ሕዝብ፣ የአካባቢውን ተራሮች፣ ሸለቆዎች እና ኮረብታዎች ደግሞ እንደ ምሽግ እና ትጥቅ በመጠቀም አሸባሪውን ቡድን ከስድስት ወራት በላይ ተፋልመዋል፤ በጠላት ላይም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል። ስቡህ ነጋሽ እንዳለው ደግሞ የሚሊሻ አባላቱ በወሰዱት የተጠና ጥቃት በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሶበታል። ማሕበረሰቡ ለጠላት ምግብ በመከልከል እና የሽብር ቡድኑ ከሚጠራው ስብሰባ ራሳቸውን በማግለል ጥላቻቸውን አሳይተዋል። በሚሊሻ አባላቱ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ይኖራሉ ብሎ የሚገምታቸውን ተራሮች፣ ሸለቆዎች እና ኮረብታማ ቦታዎች በሞርታር፣ ጂሽቃ እና ሌሎች የቡድን መሳሪያዎች ቢደበድብም ከጀግኖቹ ብትር ግን ማምለጥ አለመቻሉን ገልጸዋል። የሽቡር ቡድኑ የተወሰደበትን እርምጃ ለማርገብ እጅ እንዲሰጡ መልዕክተኛ ቢልክም ጀግኖቹ በወራሪው ቡድን ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ቀጠሉ፣ በጠላት ላይም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሱ። በዚህ ወቅትም የወረዳው ሚሊሻ ራሱን በማደራጀት የሽብር ቡድኑን እስከመጨረሻው ለማጥፋት በተጠንቀቅ ላይ መኾናቸውን ነግረውናል። አሚኮ እንደዘገበው

Source: Link to the Post

Leave a Reply