ለሻለቃ አስቻለው ቤተሰብ ትብብር እንድታደርጉ ተጠይቃችኋል! #ስለአማራ ብሎም ስለኢትዮጵያ ሲል ውድ ህይወቱን የከፈለው የሻለቃ አስቻለው ደሴ መታሰቢያ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም በደቡብ…

ለሻለቃ አስቻለው ቤተሰብ ትብብር እንድታደርጉ ተጠይቃችኋል! #ስለአማራ ብሎም ስለኢትዮጵያ ሲል ውድ ህይወቱን የከፈለው የሻለቃ አስቻለው ደሴ መታሰቢያ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ደጋመልዛ በደረንኮ ማርያም ይደረጋል። #ሻለቃ አስቻለው ደሴ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም በመንግስት የፀጥታ አካላት በእናት አባቶቹ ቤትና ፊት ላይ በጥይት በተገደለበት እለት አባቱ አቶ ደሴ ካሴ ልጅዎት ያስቀመጠውን ትጥቅና የጦር መሳሪያ አሳዩን፤ አምጡ በማለት በሌለ ነገር ቀኝ ዐይናቸው ላይ በአፈሙዝ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ገልፀዋል። ዐይናቸው አሁን ላይ እያየላቸው አይደለም፤ በዛ ላይ ህመሙ ከባድ እንደሆነ ነው የገለፁት። የሻለቃ አስቻለው እናት ወ/ሮ ጤና አለነም በባሩድና በጭስ ብቻ ሳይሆን የሚወዱትን፣አይተው ያልጠገቡትን፣ሁሌም የሚያሳሱትን ልጃቸውን በማጣታቸው በሀዘን ብዛት የሚያለቅሱበት ዐይናቸው ተጎድቷል። ከሀዘኑ በተጨማሪ የቤታቸው ከጥቅም ውጭ መሆን፣የሀብት ንብረት መውደምና መሰል ተደራራቢ ችግሮች ኑሮአቸው ጎስቋላ አድርጎባቸዋል። የጤንነታቸው ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል። በገንዘብ ችግር የተነሳ ተገቢ ህክምና ማግኘት አልቻሉም። ከሻለቃ አስቻለው ወንድም እያሱ ደሴ፣ከአባቱ ከአቶ ደሴ ካሴ እና ከእናቱ ከወ/ሮ ጤና አለነ ጋር አሚማ ያደረገው ቆይታ ምን ያህል እንደተጎዱ መረዳት ይቻላል። በእብናት ወረዳ ደረንኮ ማርያም የሻለቃ አስቻለው ደሴ አስከሬን በክብር ያረፈበት የመቃብር ስፍራውም በጅምር እንደቀረነው፤ ለማሰራት የጎደለው አቅርቦት ስለመኖሩ ተጠቅሷል። የምትችሉ ወንድም እና እህቶች ለወገኖቻችን አለንላችሁ እንድትሉ በአክብሮት ተጠይቃችኋል። #አካውንት ጤና አለነ ደጀን አባይ ባንክ 2899116151596018 #ስልክ: 090 191 8414 ጤና አለነ 092 815 7718 ሙሉዬ ደሴ

Source: Link to the Post

Leave a Reply