You are currently viewing ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ማስፋፊያ የቦሌ/ፍላሚንጎ ነዋሪዎች ያለ ካሳ ክፍያ በአሰቸኳይ እንዲነሱ ታዘዙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ…

ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ማስፋፊያ የቦሌ/ፍላሚንጎ ነዋሪዎች ያለ ካሳ ክፍያ በአሰቸኳይ እንዲነሱ ታዘዙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ ማስፋፊያ የቦሌ/ፍላሚንጎ ነዋሪዎች ያለ ካሳ ክፍያ በአሰቸኳይ እንዲነሱ ታዘዙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ መስተዳድር በመሃል ከተማ የቢሮ ግንባታዎችን እያስፋፋ ነው። በአዲስ አበባ በተለምዶ ፍላሚንጎ ተብሎ በሚጠራው የቦሌ አካባቢ ለሽመልስ አብዲሳ ፅህፈት ቤት ማስፋፊያ እንዲሆን ታስቦ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ካሳ ወይም ምትክ ቦታ በአግባቡ ሳይሰጣቸው ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ እንዲያፈርሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። በጭርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ አንድ መሬት አስተዳደር፣ የካቲት 30 ዕለት ለተነሽዎቹ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤውን የፃፈ ሲሆን፣ ስለካሳው ሲጠየቅ፣ “የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤትን አነጋግሩ” የሚል ምላሽ እየሰጠ ይገኛል። ይህን የሚለው በምን የህግ አግባብ እንደሆነ ግልፅ አይደለም። ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ለማመላከት እንደሆነ ግን ተገምቷል። የኦሮሚያ መስተዳድር በአዲስ አበባ ግንባታዎችን እያስፋፋ የሚገኝ ሲሆን፣ ለግንባታ የመረጣቸው አካባቢዎች መሃል ከተማ ያሉና በሊዝ ጨረታ የአንደኛ ደረጃ ምድብ ውስጥ የሚመደቡና ከፍተኛ ገቢ ለአዲስ አበባ ማስገኘት የሚችሉ ናቸው። ቦታዎቹ የተመረጡት እነ ሽመልስ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ አላት የሚሉትን የባለቤትነት ጥያቄ ለማጉላት እንደሆነ ብዙዎች ገምተዋል። ግንባታዎቹን አስመልክቶ ባልደራስ ክትትል እያደረገ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። መረጃ ያላችሁ ወገኖች በስልክ ቁጥር(+251) 111 268 811 መደወል ትችላላችሁ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ

Source: Link to the Post

Leave a Reply