ለባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሐፍት በባህርዳር የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪነት ድጋፍ ተደረገለት! ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ለባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ከ1 ነጥብ…

ለባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሐፍት በባህርዳር የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪነት ድጋፍ ተደረገለት! ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ለባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ካናዳ አገር ከሚገኙ በጎ አድራጊ ግለሰቦች ድጋፍ ተደርጎለታል። ድጋፉን በማስተባበር የባሕርዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር እና ካናዳ የምትኖር ሃና መንግስቱ የተባለች የባህርዳር ከተማ ተወላጅ በጎ አድራጊዎችን በማፈላለግ 1.2 ብር የሚያወጣ የመፅሐፍት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደረግ አድርጋለች። ሃናም ጁዲ ሮቢንሰተን ባገኘችው ገንዘብ የቤተ መፅሐፍ ቁሳቁሶችን ሊገዛ ችሏል። የባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሐፍት ኀላፊ ወ/ሮ ያቡንደጅ ለገሰ እንደገለፁት አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ቤተ መጻሕፍት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንዲሰጥ ተብሎ መጀመሩንም ተናግረዋል። ቤተመጻሕፍቱ ለአንባቢያን ምቹ አለመኾኑንም ገልፀዋል። አንባቢያን ተቀምጠው የሚያነቡበት በቂ መቀመጫ ወንበሮች እንደሌሉትም ተናግረዋል። እድሳት እንደሚያስፈልገውም አስታውቀዋል። አሁን የተደረገው ድጋፍ ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደሚረዳውም አስታውቀዋል። ማኅበሩ ያወቀ፣ ታሪኩን የተረዳና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ለመፍጠር እሠራለሁ ብሏል። የባሕርዳር ከተማ የበጎ አድራጎት ማኅበር ሰብሳቢ አቶ መታገስ ገብረሚካኤል ማኅበራቸው በርካታ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ እየተሳተፈ መኾኑን ገልፀዋል። አቶ መታገስ አክለውም ድጋፍ የተደረጉት ቁሳቁሶች ብልሽት እንዳይገጥማቸው ነባሩ ቤተመጻሕፍት ቤት ዕድሳት ስለሚያስፈልገው ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል። ከካናዳዊቷ ጁዲ ሮቢንሰተን ባደረጉት ድጋፍ በበጎ አድራጎት ማኅበሩ በኩል ለቤተ መፃሕፍቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል። ባሕርደር ከተማ የትምህርት ከተማ እንደምትባል ያነሱት ሰብሳቢው ከተማዋን የሚመጥን እና ለከተማዋ ማኅበረሰብ በቂ የኾነ ቤተ መጻሕፍት አለመኖሩንም ገልፀዋል። ከተማዋ ከባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት በተጨማሪ ሌሎች ቤተ መፃሕፍት እንደሚያስፈልጓትም ተናግረዋል። ከዚያ አስቀድሞ የባሕርዳር የሕዝብ ቤተ መጻሐፍት መሟላት እንደሚገባውም ገልፀዋል። ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም አስታውቀዋል። የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ማስቀመጫ ሼልፎችን ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል። ትውልዱን ለመለወጥ ትምህርት ላይ መሥራት ይገባናልም ብለዋል። ወደፊት የባሕርዳርን የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አፍርሰው እንደ አዲስ ለመገንባት እቅድ መያዛቸውንም ገልፅዋል። መጻሕፍቱን ከተማሪዎች፣ ከመምህራን እና ከቤተ መጻሕፍቱ ሠራተኞች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጥናትን መሠረት አድርገው የገዟቸው መኾናቸውንም ተናግረዋል። የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ጋሻው ቤተ መጻሕፍቱን ማዘመን የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል። የማንበቢያ ወንበሮች፣ ሸልፎችና መጻሕፍት ድጋፍ እንደተደረገላቸውንም አስታውቀዋል። ከተማዋን የሚመጥን ዘመናዊ ቤተመጻሕፍት እንዲኖር እየሠሩ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን አሻራ ዩትዩብ ቻናል ላይ ይመልከቱ! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply