
ለባጃጅ ፣ ታክሲ እና የተለያዩ መኪና አሽከርካሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ የትብብር ጥሪ‼️ መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ነገ እሁድ መጋቢት 24/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ለሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ፣የተቃውሞ ሰልፍ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ፣የታክሲ አሽከርካሪዎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ መኪና አሽከርካሪዎች በሙሉ ፦ 1).ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዐት ጀምሮ የነገው የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ ጡርንባ/ክላክስ/ በያላችሁበት ቦታ ፣መንገድ ፣በተለይም በዋና በዋና ጎዳናዎች በማሰማት ፤ሞታችን ሰርጋችን ከሚመስለው አማራ ጠል ስርዓት መፍትሄ አንጠብቅም፤ በማለት ለሚደረግው የተቃውሞ ሰልፍ ያላችሁን አጋርነት ትገልፁ ዘንድ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። 2).ነገ ጠዋት ሁሉም አሽከርካሪዎች የዚህ ሰላማዊ ተቃውሞ ተሳታፊ እንዲሆን እና በዋና ዋና አደባባዮች አሽከርካሪ ይዞ ባለመገኘት አማራዊ ትብብራችሁን ታደርጉ ዘንድ የህዝባዊ ተቃውሞ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል ። ህልውናችን በክንዳችን‼️ የባህር ዳር ከተማና አካባቢው የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post