
“ለቤተ መንግስት ግንባታ የተጠየቀ በጀት የለም፤ እየጸደቀ ያለ በጀትም የለም” የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ያደረጉት ዱላ ቀረሽ ክርክር‼ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የፌደራል መንግስት “ለአዲስ ቤተ መንግስት ግንባታ ያቀረበው የበጀት ጥያቄም ሆነ እያጸደቀ ያለው በጀት አለመኖሩን” የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡ አቶ አህመድ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በዛሬው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል መንግስት ባቀረበው 2016 በጀት ላይ ከምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የገንዘብ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች ውስጥ “ለቤተመንግስት እና ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች “እየተሰበሰበ ነው” የተባለን “500 ቢሊዮን ብር” የተመለከተው ይገኝበታል፡፡ ይህንን ጥያቄ ያነሱት የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አቶ አበባው ደሳለው፤ የገንዘብ አሰባሰቡ “የመንግስትን አሰራር እና መመሪያ” ተከትሎ እየተፈጸመ ነው ወይ ብለዋል፡፡ እኚሁ የፓርላማ አባል፤ “ይህ ብር የመንግስት ቋት ውስጥ አለ ወይ?” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ለዚህ ጥያቄ የተወሰነ ማብራሪያ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ከሌላው የአብን የፓርላማ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ተቋርጧል፡፡ “የስነ ስርዓት ጥያቄ” ያነሱት አቶ ክርስቲያን፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ የሚሰጡት ምላሽ የምክር ቤቱን “የህግ እና የስነ ስርዓት ጉዳዮችን የጣሰ” እንደሆነ ገልጸው “እርምት እንዲደረግ” ጠይቀዋል፡፡ ethiopianinsider እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:-Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post