
ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ገቢ እንዲደረግ የኦሮሚያ ክልል ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ድርጅቶች ግለሰቦች በድርቅ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጠው የቦረና ህዝብ እርዳታ እያሰባሰቡ ይገኛሉ፡፡
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን ጉዳይ ለማቀናጀት ከክልል እስከ ቀበሌ ድርስ ድጋፉን የሚያስተባብር መዋቅር የዘረጋ በመሆኑ፣ ለድጋፉ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የሂሳብ ቁጥር የተከፈተ በመሆኑ እና እየተሰበሰበ ያለው ድጋፍ ተጠያቂነትና ኃላፊነት ባለው መልኩ እንዲሰበሰብ ብሎም ተጋላጩ ህዝብ ጋር እንዲደርስ በተለያየ አቅጣጫ ለተጎጂው ህዝብ እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ ወደተከፈቱ የባንክ አካውንቶች እንዲገቡ ተይቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
ሲንቄ ባንክ፡ 1029565101201
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000007343756
ላይ ገቢ እንዲደረግ ጥሪውን አቅረቧል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post