ለተመድ አድርሱልን!!! ከወለጋ አንገር ጉትን (ከአጉልዞ ጥያቄ ) ስቶክሆልም :- ሰኔ 26/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወ…

ለተመድ አድርሱልን!!! ከወለጋ አንገር ጉትን (ከአጉልዞ ጥያቄ ) ስቶክሆልም :- ሰኔ 26/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ በአርቁቢ መንደር 1-6 ቀበሌዎች እና ከወረዳው ከፊጢበቆ ቀበሌ እንድሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሶጌ ወረዳ ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች እና በሶጌ ( ምዥጋ) ወረዳ ስር ከሚገኙት በሊሙ ወረዳ የሚያዋስኑ አጠቃላይ የአማራ ማህበረሰብ ህዝቦች ከተፈናቀሉ 2 ዓመት አለፋቸው። ተፈናቃዮቹ በአማራ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የተጠለሉ ቢሆን በመንግስት በኩል በያዝነው ወር ሰኔ 10 እስከ 15 ባለው ጊዜ ውስጥ ለመመለስ ቃል ቢገባም እስካሁን እንዳልተመለሱ ተፈናቃዮች ገለፁ። በሊሙ ወረዳ በአርቁቢ ቀበሌ በአከባቢው ላይ ከአማራ ማህበረሰብ መፈናቀል ዋነኛ ምክንያት ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን ድረስ ባሉ የፖለቲካ አመራሮች እንደሆኑ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በባዶ እጃቸው ከወጡበት የአርቁምቢ ቀበሌ ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው መንግስት አስቸኳይ ምላሽ እንድሰጣቸው ተማፅነዋል። በሁለት አመታት ውስጥ ማለትም ከ2011ዓ.ም – 2013ዓ.ም ብቻ ከሁለቱ ክልል በተጠቀሱት አጎራባች አከባቢዎች ብቻ ከ250ሺህ በላይ የአማራ ተፈናቃዮች ወደአማራ ክልል መሠደዳቸውን ከቦታው ከሚገኙ ከተፈናቃዮቹ ተወካዮች ያገኘነው መረጃ ያመረክታል። አጠቃላይ ከተጠቀሱት አከባቢዎች ብቻ የተፈናቅለው የተጠለሉበት፦ 1- ቡሬ 18000 ሺህ 2- ቋሪት 67000 ሺህ 3- ደጋ ዳሞት 36000 ሺህ 4- ሠከላ 23000 ሽ 5- አዴት 18ዐዐዐ ሽ 6- ጎንጂ 13000 7- ፍኖተ ሠላም 80000ሽ 8- ደበጫ 22000 ሽህ ሲሆኑ ** ተጨማሪ ያልተመዘገቡ ከሊሙ ወረዳ፣ ከጊዳ አያና፣ ከኪረሙ ወረዳ፣ ከአሙሩ ወረዳ፣ ከጉቶ ጊዳወረዳ፣ አቤደንጎሮ ወረዳ፣ እና ከሌሎች አከባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት የተፈናቀሉ የአማራ ማህበረሰብ ህዝቦች የመረጃ ዳታው ከሚሠጥበት ነው የሠበሠብኩት። ያልተመዘገበ ከሁሉም 50000 ሽህ በላይ ይኖራል ሲሉ የተፈናቀሉ ተወካዮች ገልጸዋል። በምስራቅ ወለጋ በአርቁምቢ ቀበሌ ከመንደር 1-6 ባሉ በርካታ ቁጥር ካላቸው የአማራ ሰፈሮች አከባቢውን በበላይነት ለመፈናቀል ምክኒያት ናቸው ያሏቸው የየቀበሌው ሊቀመንበሮችና የቀበሌ ማናጀሮች ስም ዝርዝር አያይዘውም ገልጸዋል። ከነዚህ ለአማራ ማህበረሰብ ህዝቦች መፈናቀል ከፍተኛ ሚና ነበሯቸው ከሚባሉት ከብዙዎቹ ጥቂቶች መካከል፦ 1ኛ- ነጋሳ . ፈይሳ 2- ዳባ ነመራ 3- ታከለ ነጋስ 4- ቢቂላ ዳባ 5- ማሞ በቀለ 6- በርሔ ንጉስ 7- መሠረት በቀለ የሚባሉ ሲሆን የአርቁምቢ መንደር 1 ቀበሌ ከተማ ሊቀመንበር አቶ መሠረት በቀለ የሚባሉ ሲሆን፦ ጣባ፥ የቢቂላ አባት ነው። ነጋሳ፥ የታከለ አባት ነው። በርሔ ንጉስ የተባለው ግለሰብ ደግሞ #ማሬ የሚባል የአማራ ምስኪን ገበሬ በካራ ያረዳ ሠው ነው። ሲሉ ለአጉልዞ ጥያቄ ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። #sayenouph #Stopa_Amhara_Genocide #StopAmharaGenocide #በቃን #AmharaGenocide #እምቢ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply