ለተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ አቶ መላክ መኮነን ለአሐዱ እንዳሉት በመንግስት ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት እንዲያገኙ ለማድረግ ምዝገባ ሊያደርግ ነው፡፡የልደት ሰርተፍኬት ካለው ግለሰባዊ እና ሀገራዊ ጠቀሜታ አንጻር ምዝገባውን በሁሉም ወረዳ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ባሉበት የሚመዘገብ ይሆናል ብለዋል፡፡

ስራው ከወሳኝ ኩነት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር እና ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚችል የገለፁት አማካሪው ምዝገባው ከታህሳስ 26 /2013 ዓ.ም እስከ ጥር 20/05/2013 ዓ.ም ይጠናቃል ብለዋል ፡፡

የአሰራር መመሪያውን ተከትሎ በትክክል መመዝገብ እንዲቻል ትምህርት ጽ/ቤት እና ርዕሰ መምህራን በተሰጣቸው ግንዛቤ መሰረት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡አማካሪው ከዚህ ቀደም አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ግዜ የታገደ መሆኑን አንስተው ከታህሳስ 20 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ እገዳዉ ተነስቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

***************************************************************************

ዘጋቢ፡ሰላም በቀለ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply