
ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እንጂባራ ዩኒበርስቲ የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መሆኑ ተሠማ‼ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡ በዕለቱም ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው ያረጋገጡት፡፡ ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፥ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡ በተጨማሪም በኪነ-ጥበብ ሥራወቿ÷ የአዊን ሕዝብ ቋንቋ እና ባሕል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ ይበረከትላታል ማለታቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡ የምረቃ እና የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ሥነ- ሥርዓቱ በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ ለጂጂ የሚሰጠውን የክብር ዶክትሬት እና የተማሪዎቹን የምርቃት ሥነ- ሥርዓት በማስመልከት የፊታችን ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ለመገናኛ ብዙኃን ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post