‹‹ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣ ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም ቀን አይምጣ፡፡››

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
የኢትዩጵያ ገበሬዎች ትራክተር ከሚገዛ፣ ክላሸን ኮቨ በመቶ ሽህ ብር ይገዛል!!!
ፀ/ት ፂዮን ዘማርያምና ሚሊዮን ዘአማኑኤል
‹‹ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣
ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም ቀን አይምጣ፡፡››

ለዳኛ ፍሬህይወትና ለዳኛ ወልደሚካኤል ዘብ እንደቆሙልን ዘብ ልንቆምላቸው ይገባል እንላለን፡፡ የህግ ሉዓላዊነት ሳየከበር፣ ልማት የለም፣ ገበሬው ትራክተር ከሚገዛ፣ ክላሸን ኮቨ በመቶ ሽህ ብር ይገዛል!!! ዶክተር አብይ መንግሥትና ጋዜጠኞች፣ ለምን ካላችሁ፣ ከፕሬስ ኮንፍረንስ ገበታችሁ ተነስታችሁ ገበሬዎቹን ጠይቆቸው!!! ክላሸን ኮቨ ለፖለቲካ ነጻነት፣ ህልውናውን ለማስጠበቅ፣ ትራክተር ለኢኮኖሚ ነጻነት ብሎ ምርጫው አድርጎታል፡፡ የዚህ ሁሉ ህዝብ መፈናቀል የተረከብኩት 1.7 ሚሊዮን ህዝብ በህወሓት ተፈናቅሎ ነው፡፡ በእኔ ጊዜ 1.5 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ ነው የተፈናቀለው፡፡ ይሄ በሂደት ቡና እንደሚሰክን ይሰክናል ወዘተ ባሉት ገለፃ አንስማማም፡፡ የፌዴራል መንግሥት የህዝብ መፈናቀልን ማስቆም እንደማይችል በራሱ ጊዜ እንደሚሰክን ተስፋ ቢያደርጉም፣ የኢትዩጵያ ገበሬዎች ትራክተር ከሚገዛ፣ ክላሸን ኮቨ በመቶ ሽህ ብር ይገዛል!!!
የህወሓት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት በሃገሪቱ ዴሞክራሲን የማስፈን ቁመና መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ይሆናል፡፡ ከግንቦት 1983ዓ/ም ጀምሮ በትረ ሥልጣኑን የያዘው የህወሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት በብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ግንባርነት በዘር ላይ የተመሠረተ ህገ-መንግሥት በህዝብ ላይ በመጫን ዘር ተኮር ፌዴራሊዝም በማዋቀር፣ በፌዴራልና በክልል መንግሥታቶች በማዋቀር የዘር ክልሎች ወሰንና ድንበር ያለህዝብ ይሁንታ በማካለል የሃገሪቱን ህዝብ በማያባራ ጦርነት በመክተት፣ አናሳው ህወሓት/ኢህአዴግ በትረሥልጣኑን ላለፉት 27 አመታት በማስቀጠል ቆይቶ ሚኒማውን ማሞላት ስላልቻለ፣ በትረሥልጣኑን ለኦህዴድ/ ኢህአዴግ በማስተላለፍ የመለስ ርአይና ውርስን ማስቀጠል ችሎል፡፡ ለኦህዴድ/ ኢህአዴግ ተሠፍሮ የተሰጠው ሥልጣን አንደኛ የበሰበሰውን ህገመንግሥት ማስቀጠል፣ ሁለተኛ አብዬታዊ ዴሞክራሲን ማስቀጠል ሦስተኛ ልማታዊ መንግሥትን ማስፈን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ-ካርታው ይህ ነው፡፡ ወዶገባ 107 ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንዳችም መደራደሪያ ፍኖተ ካርታ ሳይነድፉ በቦሌና በባሌ እንዳወጣጣቸው ወደ ሃገር ገቡ፡፡
የመለስ ቅርሰ ውርስ ይቀጥላል፣ ‹‹የመቶ አመት የቤት ሥራ!!!›› የፖለቲካ በትረ-ሥልጣኑ ከህወሓት/ኢህአዴግ ወደ ኦህዴድ/ኢህአዴግ የዘር ጦር አበጋዞች መንግሥት ተዘዋውሮል፡፡ የህወሓት ፓርቲ የፖለቲካ የኢከኮኖሚ ስልጣንና ጥቅም በኦህዴድ ፓርቲ የፖለቲካ የኢከኮኖሚ ስልጣን ይቀጥላል፡፡ በሚቀጥለው የ2012ዓ/ም አምስተኛ ዙር ምርጫ ኢህአዴግ ወደ ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲነት›› ስሙ ተቀይሮ፣ በትግራይ ክልል ህወሓትና አረና፣ በኦሮሚያ ክልል ኦህዴድና ኦነግ፣ በአማራ ክልል ብአዴን አብን፣ በደቡብ ክልል ደኢህዴን ሲአን፣ አፋር አብዴፓ፣ ሶማሌ ሶሕዴፓ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ ቤጉሕዴፓ፣ ጋምቤላ ጋሕአዴን፣ሐረሪ ኦሕዴድ/ ኢሕአዴግ/ ሐብሊ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ኦሕዴድ/ ኢሕአዴግ/ሐብሊ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኢሕአዴግ/ ሶሕዴፓ፣ አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ኢሕአዴግ ምርጫውን ያሸንፋሉ፡፡ በዘር ላይ የተመሠረተው ህገመንግሥት ዳግም ይፀድቃል፣ አብዬታዊ ዴሞክራሲ የፓርቲው ርዬት ሆኖ ይቀጥላል፣ ልማታዊ መንግሥት የኢኮኖሚ መመርያ ሆኖ የመለስ ራዕይ ይቀጥላል፡፡
• የዳክተር አብይ አህመድ የኦህዴድ/ኢህአዴግ መንግሥት፣ ከዘር ተኮር የፖለቲካ ወኪል እንጂ የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ መሆን አይቻላቸውም፡፡
ከ2012ዓ/ም ኦህዴድ አብይ መንግሥት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የሥልጣን ተዋረዱን በፌዴራልና በክልል መንግሥቶች ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር እንደ ሕወሓት ተረኛ መንግሥት በመሆን ሃገሪቱን ይቆጣጠራል፡፡ የሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ፣ መንግሥታዊ መዋቅር ቢሮክራሲው፣ የፋይናንስ ባንክ ዘርፎች፣ የመሬት ኃብት ፣ የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች ኃብት ማበብ፣ የሚንስትሮችና ዲፕሎማቶች ሹመት በአመዛኙ በኦሕዴድ ኦሮሞዎች ይያዛል፡፡ በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግሥት አስተዳደሮች ቁጥር ይበራከታል፣ የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ወዘተ መንግሥቶች እስከ 20 ክልላዊ መንግሥትነት ያሻቅባሉ፡፡ ቀሪዎቹም ከወረዳ ፣ አውራጃ፣ ዞን ፣ ልዩ ዞን፣ እየተባሉ አስተዳደራዊ ሥልጣን ያገኛሉ፡፡ አማርኛና ኦሮሞኛ ብሄራዊ ቆንቆ ይሆናሉ፡፡ ክልላዊ መንግሥቶች የራሳቸው የፖሊስ ኃይል፣ ሚሊሽያ፣ ደህንነት ወዘተ፣ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቨዝንና ሬዲዬ ጣቢያ፣ ዘር ተኮር የባንክና ኢንሹራንሰ አደረጃጀት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ወዘተ አደረጃጀት ይቀጥላል፡፡ ኦህዴድ/ ኢህአዴግ በምርጫ እስኪያሸንፍ ድረስ የህዝብ መፈናቀል ይቀጥላል፣ የአብይ መንግሥት ህግና ሥርዓት እንደሌለና የፌዴራል መንግሥት በክልል መንግሥት ሥራ እንደማይገባ አስሬ በመግለፅ ኦህዴድ/ኢህአዴግ ተፎካካሪ 107 ፓርቲዎች በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ተንቀሳቅሰው መስራት ባለመቻላቸው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት አይኖርም የክልል መንግሥቶች የኮንትሮባንድ፣ ህገወጥ የድንበር ንግድ፣ የወርቅ፣ የሰሊጥ፣ የቡና፣ የእንሰሳ ኃብት ወዘተ አጎራባች ሃገራት መሸሽ፣ የመሥሪያ፣ የገንዘብ፣ የመድኃኒት ህገወጥ ዝውውር መጨመር፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የፋይናንስ የባንኮች ውድቀት፣ የግብር መሰብሰብ ብቃት ማነስ፣ በአጠቃላይ በአንድ አገር አራት መንግሥት መኖር ኢኮኖሚው ከአረንቃ ወደ አረንቆ ይሸጋገራል፡፡ የአንድ አገር ኢኮኖሚ በልመና አይመራም፣ የቪዝን ኢትዮጵያ ምሁራን ጥናታወ ምክርን ብንቀበል ሃገራችን በአጭር ጊዜ ወደ ልማት ጎዳና ትሸጋገራለች፡፡
የህብረ-ብሔር ድርጅቶችና ፓርቲዎች በዜግነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተከታይ የማግኘትና የፖለቲካ ሥልጣን የመወዳደርና የማሸነፍ እጣ ፈንታቸው በ2012ዓ/ም ምርጫ የቀጨጨ በመሆኑ ራሳቸውን ከምርጫ የማውጣት ስልት ሊከተሉ ይችልሉ፡፡
ከ2012 ዓ/ም አመት ሁለት አመት ቆይታ በኃላ ክልላዊ የዘር አደረጃጀት ለህዝቡ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ችግር መፍታት ባለመቻላቸው፣ የፖለቲካ ሥልጣን ጥያቄ፣ የኢኮኖሚ የዶቦ ድርሻ ጥያቄና የሥራ አጥነት ችግር መፍታት አለመቻል፣ እንዲሁም የማህበራዊ የጤና፣ የትምህርት ቤት፣ የመንገድ፣ የመብራት፣የውኃ፣ የስልክ ወዘተ ሽፋን ድርሻ ፍህታዊ አለመሆን ጥያቄ ተበራክቶ የክልላዊ መንግሥቶች ወደ አውራጃ መንግሥትነት መፈረካከስ ይከተላል፡፡ ከ2012ዓ/ም በኃላ ህዝባዊ ትግልና አመፅ ከክልላዊ ምንግሥት ወደ አውራጃ ግዛታዊ መንግሥትነት ይከሰታል፣በዚህም መሠረት-
{1} በትግራይ ክልል ውስጥ፣ መቐለ፣ ሽሬ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ወዘተ አውራጃ ግዛታዊ መንግስትነት ይሸነሸናሉ
{2} በአማራ ክልል ውስጥ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ አውራጃ ግዛታዊ መንግሥትነት የሸነሸናሉ
{3} በኦሮሚያ ክልል ውስጥ፣ ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ ወዘተ አውራጃ ግዛታዊ መንግሥትነት ይሸነሸናሉ
{4} በደቡብ ክልል ውስጥ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሃዲያ፣ ጌዲዬ፣ ጉራጌ፣ከፋ፣ጋሞ፣ ወዘተ አውራጃ ግዛታዊ መንግሥትነት ይሸነሸናሉ
{5} በአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ ክልሎች ውስጥ፣ ወዘተ አውራጃ ግዛታዊ መንግሥትነት ይሸነሸናሉ
• የህብረ-ብሔር ድርጅቶችና ፓርቲዎች በዜግነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ
በ2017ዓ/ም ሰባተኛው ምርጫ የህብረ-ብሔር ድርጅቶችና ፓርቲዎች በዜግነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተከታይ የማግኘትና የፖለቲካ ሥልጣን የመወዳደርና የማሸነፍ እጣ ፈንታቸው እያደገ ይመጣል፡፡ የብሄር ፓርቲዎች ህዝባዊ ድጋፍ እየሞሸሸ ይሄዳል፡፡ ጠንካራ የሲቪክ ድርጅቶች ያብባሉ፣ የዴሞክራሲያዊ ተቆማት ይጠናከራሉ፣ ምርጫ ቦርድ፣ የፍርድ ቤት፣ የፖሊስ፣ እንባ ጠባቂ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወዘተ የዴሞክራሲያዊ ሂደት በሰው ህሊና የማስረፅ፣ የብዙ ወጣቶች በከፍተኛ ትምህርት ዮኒቨርሲቲዎች ውስጥ የእውቀት ልቀት ምጥቀት መበራከት፣ በኢኮኖሚ እድገት የከተሜነት ድርሻ ከመቶ 20 የነበረው ቢያንስ 50 በመቶ ለሚቀጥሉት 50 አመታት ከደረሰ ብሄር ብሄረሰቦች በከተማዎቸ ውስጥ የመቅለጥ፣ የመዋሃድ፣ የመጋባት ትስስር እያደገ ይመጣል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተሞች በምርጫ የእራሳቸውን ከንቲባ እየመረጡ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው መከበር ይኖርበታል፡፡ አዲስ አበባ፣ (3,273,000 እስከ 3,352,000 ሲገመት ከዚህም በላይ ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን የሚገምቱ ህብረ ብሄር ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ዓይነት በሌሎች ክልሎች ከተሞች ማበብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሃገሪቱ ውስጥ ከመቶ ሽህ በላይ ህዝብ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ጎንደር (323,900 እስከ 341,991)፣ መቀሌ (323,700 እስከ 340,859)፣ ባህር ዳር (187,900-198,428)፣ ጂማ (177,900-186,148)፣ ጂግጂጋ (159,300-164,321)፣ ሻሸመኔ (147,800- 154,587፣ ሶዶ (153,322)፣ ብሸፍቱ/ ደብረዘይት (147,100- 153,847)፣ አርባ ምንጭ (142,900-151,013)፣ ሶዶ (145,100)፣ ሆሳዕና (133,800-141,352)፣ ሀረር/ሀረሪ (129,000-133,000)፣ ዲላ (112,900-119,276)፣ ነቀምት (110,640-115,741)፣ ደብረ ብርሃን (102,100-107,827)፣ ደብረ ማርቆስ (103,263)፣ አሰላ (103,522)፣ ከተሞች፣ የአዲስ አበባን ተምሳሌት በማድረግ፣ ከተሞቻቸውን ህብረ ብሄር ሰዎች የሚኖሩባቸው፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በፈለጉበት ቦታ ኃብት ማፍራት፣ ተዘዋውሮ የመስራት፣ ወዘተ እነዚህ ከተሞች አስተዳደር ዜጎችን የመሳብ አብሮ የመኖር፣ በህብረት ኢንቨስት በማድረግ፣ የአገር ውስጥና የባህርማዶና ኢንቨስተሮች በከተሞቻቸው ውስጥ እንዲሰሩ በማድረግ ወደ ሥልጣኔ ማማ በህብረት በጋራ ማደግ ይቻላል እንላለን፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የደቡብ ክልል ህዝቦች ማህበር ስብሰባ ያካሁዳሉ፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ የህወሓት ደጋፊዎች ስብሰባ ያካሂዳሉ፣ የሀረሪ፣ የሱማሌ ወዘተ የአዲስ አበባ ኖሪዎች ስብሰባ የማድረግ መብት ሲኖራቸው የአዲስ አበባ ህዝብ ከቀበሌ፣ ወረዳና ክፍለ ከተሞች ተደራጅቶ መሰብሰብና ስለከተማዋ መወያየት መብት የለውም ይህን የተረዱ ወጣቶች የአዲስአበባን ወጣቶች የማደራጀት የበመብት ጥያቄ በታዋቂው የመብት ተሞጋችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መሪነት የዴሞክራሲ አብሪ ጥይት በባልደራስ አዳራሽ የተከናወነው፡፡ ጥያቄው የመደራጀት የመብት ጥያቄ ነው፣ ጥያቄው ሰላማዊ ትግል ነው፡፡ ጥያቄው የከተማው ህዝብ በምርጫ የራሱን ከንቲባ እንዲመርጥ የሚያሰናዳ ህዝባዊ ተሳትፎ እዲጨምር የሚያደርግ ቅስቀሳ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ከቀበሌ እሰከ ክፍለከተማ የሚያስተዳድሩት ያልመረጣቸው ሹመኞች የመከራ ገፈት ቀማሽ በመሆን የልማት ተፈናቃይ፣ የቤት ኪራይ በአድሎና በሙስና የሚሰጥበት የወሮበሎች ከተማ መሆን፣ የመንግሥት ቤት ተከራይተው የራሳቸውን ቤት የሚያከራዩ ሹመኖች ከተማ መሆን፣ በባንክ ብድር ቆጥበው ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሰሩ ነዋሪዎች ሃብትና ንብረት በኦህዴድ፣ ኢህአዴግ የዘር ተኮር ድርጅት መነጠቁ ህግ የሌለበት ህወሓት፣ ኦህዴድ ስልቻ ቀልቀሎ የተረኛና የፈረቃ የዘር ተኮር አስተዳደር አይቀጥልም ከተደራጀን የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጣቢዎች ባንክ፣ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን በፍርድ ቤት ገትሮ መከራከር ይችላል፡፡ ከተደራጀ የአዲስ አበባ ህዝብ ከተማዋን ፀጥታ የሚጠብቁ የፖሊስ ኃይል ከእራሱ አብራክ በወጡ ልጆቹ የመጠበቅ ሙሉ መብት ይጎናፀፋል፡፡ ከተደራጀ በከተማው ያለ የመሣሪያና የገንዘብ ድርጅት፣ የኮንትሮባንድ ህገወጥ ንግድ ሁሉ ይጠፋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ህዝብ 40 ቢሊዮን ብር ግብር የሚከፍለው ሃብትና ንብረት ሲሆን መብቱን ማስከበር ዴሞክራሲያዊ ጸጋው ነው፡፡ ድሬዳዋ፣ ሃረሪ፣ አዳማ፣ ሃዋሳ ከተማ ህዝቦች ለመብታችሁ ታገሉ፡፡ የህወሓት የድሬዳዋ 40/40/20 ድልድል የአፓርታይድ ሥርዓት ሊመነገል ይገባዋል እንላለን!!!
የኦህዴድ/ ኢህአዴግ በሃገራችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡
አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡
ሁለተኛው መሠረታዊ የኢኮኖሚ ነፃነት መመዘኛ የመንግሥትን የፊስካልና የወጪ አቅም የሚመለከት ነው፡፡ መንግሥት ምን ያህል ታክስ ይሰበስባል; ምን ያህል ወጪ ያደርጋል; የሚሉት መመዘኛዎች በዚህ መሰረት የሚቃኙ ናቸው፣የታክስ ገቢው ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 17 በመቶ ለማሳደግ ከፍተኛ የታክስ አስተዳደር ጥረት ለማድረግ ቢታሰብም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተነሳ ህዝባዊ አመፅ ግብር የመሰብሰብ ችግር ገጥሞታል፡፡ የፊስካል ፖሊሲና የመንግስት ፋይናንስ አፈፃፀም፣‹‹ጠቅላላ የታክስ ገቢ በ2002 ከነበረበት 43 ቢሊዩን ብር በ2006 መጨረሻ ወደ 133 ቢሊዩን ብር ከፍ ያለ ሲሆን የታክስ ገቢው ባለፍት አራት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ በ33 በመቶ አድጎል፡፡ የተሰበሰበው ገቢ በራሳ አቅም ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማካሄድ አስችሎ ነበር፡፡ በ2007 በጀት ዓመት የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት ያለውን ድርሻ ወደ 15 በመቶ ለማድረስ የታቀደ ቢሆንም በ2006 የበጀት ዓመት የተሰበሰበው የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 12.7 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት አማካይ አፈፃፀም 15 በመቶ ነው፡፡ ከመንግስት ጠቅላላ የወጪ በጀት ውስጥ ወደ 60 በመቶው የሚጠጋው ለካፒታል ኢንቨስትመንት ሲደለደል የቆየ ሲሆን፣ቀሪው 40 በመቶ ገደማ ብቻ የመደበኛ ወጪ ለመሸፈን ሲመደብ ቆይቶል፡፡ በዕቅድ ዘመኑ የተሰበሰበው የመንግስት ገቢ በመደልደል የበጀት ጉድለቱ ከ3 በመቶ እንዳይበልጥ በማድረግ ጥብቅ የፊስካል ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ታቅዶ ነበር፡፡ በ2008ና በ2009ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና በአማራ ህዝባዊ ተጋድሎ የግብርና የታክስ መሰብሰብ ዕቅድ ‹ላም አለኝ በሰማይ ፣ወተቶንም አላይ› ሆነ፡፡ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ ያልቻለ መንግሥት በህዝብ የተጠላ መንግሥት ነው፡፡ የስልጣን እድሜውም አጭር ነው፡፡ ህወሓት ከህዝብ ግብር መሰብሰብ ካልቻለ ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ለፖሊስ፣ለደህንነቱ፣ለፊዴራልና ለክልሎች ለሲቪል ሠራተኞችና አስተዳደር የሚከፈል ደሞዝ ስለማይኖር ከሥልጣን መንበሩ ይወገዳል፡፡
ሦስተኛው የኢኮኖሚ ነፃነት መመዘኛ ኢኮኖሚው እንዴት እንደሚተዳደር የሚያሳይ ሲሆን፣በኢትዩጵያ መንግሥት ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ስም መንግሥታዊው ዘርፍ የግሉን ዘርፍ ኃብትና ሊሠራ የሚችለውን ኢንቨስትመንት ሥራ ሁሉ በመሻማት የግሉን ዘርፍ እድገትና ሚና አጨናግፎታል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በማስፋፋት ህወሓት ኢፈርት፣ብአዴን ጥረት፣ ኦህዴድ ዲንሾ እና ደኢህዴን ወንዶ የንግድ ድርጅቶችን በተጠናከረ መልክ በዶክተር አብይ መንግሥት የአንድ አመት ቆይታ ቀጣይነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ ተፋካካሪ ፓርቲዎች የኦህዴድ/ኢህአዴግ መንግሥትንና የምርጫ ቦርድን ፓርቲዎች ከንግድ ድርጅት ሥራ እንዲወጡ አለመጠየቃቸው ቀጣዩ ምርጫ ነፃና እንከን የለሸ ሆኖ ይጠናቀቃል፡፡ የኢትዩጵያ መንግሥት ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ነው ወይስ ‹‹የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት›› ነው የሚለውን የኢትዩጵያ የፖለቲካ ኃይሎች አቆም መውስድ ይገባቸዋል፡፡ አሊያም በኢትዩጵያ ያለው መንግስት ምን ዓይነት መንግስት ነው የሚለው በጥናት ተደግፎ መቅረብ አለበት፡፡ በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመመስረት የብዙሃን ፓርቲዎች የውድድር ሥርአት ሠፍኖ፣ በህዝብ ድምፅ አሸናፊው ሥልጣን የሚይዝበት የምርጫ ስርዓተ-አሥተዳደር መገንባት አለበት፡፡
የመንግሥት የልማት ኢንተርፕራይዞች፡- በመንግስት የሚተዳደሩ ድርጅቶች የሙስና መፈልፈያዎች፣የእውቀትና የብቃት ችግር የተንሠራፋባቸው፣ በሥልጣን በመጠቀም የግል ፍላጎት ተጠቃሚነትን የሚያስፋፉ፣ እንዲሁም ከለላን የሚያበረታቱ፣ የፖለቲካና የዝምድና አሰራር የነገሰበቸው ናቸው፡፡ ንግድን ከመፍጠር ይልቅ ፍሰቱን የሚቀለብሱ ተቆማት ናቸው፡፡ በዚህም የንግድ መዛባትን በመፍጠር፣ውድድርን በማክሰም፣በመንግሥት እጅና ጥበቃ ከውድድር ውጭ ሆነው የሚተዳደሩ ድርጅቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በነፃው ንግድ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ተመሳሳይ ድርጅቶች እንዲቆቆሙ ማድረግ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት አስፈላጊ ነው፡፡
አራተኛ ኢኮኖሚው ለዓለም ገበያ ክፍት መሆን፣የንግድ፣የኢንቨስትመንት፣እንዲሁም ባንኮችና መድህን ድርጅቶች በተመለከተ፤- በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ጠቅላላ የመንግሥትና የግል ኢንቨስትመንት ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ 41.3 በመቶ እንዲሆን ተገምቶ ነበር፡፡ ከጠቅላላ ኢንቨስትመንቱ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛውን በአገር ውስጥ ቁጠባ ለመሸፈን እንዲቻል በዕቅድ ዘመኑ የአገር ውስጥ ቁጠባ ምጣኔን ወደ 29.6 በመቶ ለማድረስ ግብ ተጥሎ ነበር፡፡ ሆኖም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተነሳ ህዝባዊ አመፅ የሃገር ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ንብረት የሆኑ ፋብሪካዎችና እርሻዎች መውደም ምክንያት የታቀደው አልተሞላም፡፡ በመቀጠልም ከ2008 እስከ 2009ዓ/ም የውጭ ንግድ ገቢ አሽቆለቆለ፣ በአንጻሩ የገቢ ንግድ ወጪ በማደጉ የንግድ ሚዛኑ ተናጋ፡፡ በዚህም የተነሳ ያልተረጋጋ የብር ምንዛሪ ተመንና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት፣የመንግሥትና የልማት ድርጅቶች በዕዳ ክፍያ ጫና ተሰነጉ፡፡ በአጠቃላይ የአገሪቱ የፋይናንስና የባንክ ኢንዱስትሪው ልማቱ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የማቅረብ ብቃት ወደቀ፡፡ በሃገሪቱ የፋይናሻል ዘርፍ ውድቀትና ኪሣራ ደርሶባቸዋል፡፡ የመንግሥታዊው ንግድ ባንክ፣ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ፣የኢትዩጵያ ልማት ባንክ ከባድ ኪሣራ ደርሶባቸዋል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ገንዘብ እንደ ወረቀት በማተም፣የዋጋ ግሽበቱንና የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ የውጪ ንግድ ገቢ በድርቅ ተመቶል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በጣም ተባብሶል፣በእጥረቱ ምክንያት የኮንስትራክሽን ስራዎች በአብዛኛው ተቆርጠዋል፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቆመዋል፣በሃገሪቱ በታወጀው ‹አስቸካFይ ጊዜ አዋጅ› የተነሳ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሽሽት የተነሳ፣ ይደረግ የነበረው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት አሽቆልቁሎል፣ የሆቴልና ቱሪዝም ገቢም ነጥፎል፡፡

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (INSA) ቪላድሜር ፑቲንም ኬጂቢ ነበሩ!!!
Information Network Security Agency (INSA) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያምና ሚሊዮን ዘአማኑኤል
‹‹ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣
ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም ቀን አይምጣ፡፡››

ኢሣት በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች ያላሰለሰ የመረጃ ምንጭ በመሆን ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ በመሆን ሲያገለግል አመታት አስቆጥሮል፡፡ ሆኖም ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET-ECONOMY መጣጥፎች ከአገር ውስጥ የምጣኔ ኃብት ሙያተኞች በተለያዩ ድረ-ገፆች ማለትም በሳተናው፣ አባይ፣ ዘሃበሻ፣ ኢትዮጵያ ኤክስፕሎለር፣ አትዮሚዲያ ወዘተ ድረገፆች ለብዙ አመታት ሽፋን አግኝቶል፡፡ ከማንም በላይ ብዙ አንባቢዎች ለማግኘቱ የድረ- ገፆቹ ባለቤቶች ምስክርነታቸውን ሊሰጡ ይገባል እንላለን፡፡ ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ለኢሣት ጋዜጠኞች ለአበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እንዲያሳትመው በመፍቀድ፣ በዛ ክፉ ዘመን የደረሰ ጥናታዊ መጽሃፍት ሲሆን በኢሣት ፕሮግራሞች አልቀረበም፡፡ የኢት- ኢኮኖሚ ፁሁፎችና መጽሃፍቶች በብዙ ድረ-ገፆች ሽፋን ያገኙ ሲሆን በኢሣት አለመቅረባቸው የመረጃዎቹ አስተማኝ ስላልሆኑ ታስቦ ከሆነ መልስ ሊሰጥበት ይገባል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ ዋነኛ ዓለማ በኢኮኖሚው ዘርፍ ለሃገርና ለወገን በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፁሑፍ በማቅረብ በተለያዩ ድረ-ገፆች ተደራሽነት በማግኘታችን ደስተኛ ከመሆን ሌላ እስከመቃብር እውቅና ያማንሻ በብዕር ስም ብቻ የምንታወቅ ስንሆን ከአመታት በፊት፣ ከለውጡ በፊት፣ ኢሣት በምጣኔ ኃብት የቀረቡ መጣጥፎችን ባለማስተናገዱ፣ የተጎዳው የሃገራችን ህዝብና ምሁራን ሲሆኑ አበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እጅ የሚገኘው መፅኃፍት ጥናታዊ ሥራ ዛሬ በተለያዩ ድረ-ገፆች ተለቀው በመነበብ ላይ ሲሆኑ፣ የጋዜጠኝነት ሥራችሁን ባለመወጣታችሁ ገንቢ ሂስ ለማቅረብ በማሰብ ከዓይናችሁ ጉድፍ ለማውጣት የታለመ ነው፡፡ በጋዜጠኝነት ሥራና ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ ግልፅነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ናቸው እንላለን፡፡ ኢሣት መረጃ ከውስጥ ላበረከቱ ጸሃፊዎች ምስጋና ቢቀር እንደ ነፃ ሚዲያ የማቅረብና የመዘገብ ሥራ ልክ እንደ የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (INSA) ከሃገር ውስጥ የተላከ መረጃ ኢሣት ያለ በቂና ሚዛናዊነት በጊዜው አለመዘገቡ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የቀረበው ትንተና አሳማኝ ሆኖ አላገኘንውም፡፡ ከሰባት አመታት በፊት በኢሣት ጋዜጠኞች መረጃው ይቅረብ አይቅረብ የነበረ ክርክር ይፋ ቢደረግ ታላቅነታችሁን ያበስርላችሆል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ሥራዎችን በኢሣት በፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና በኢሳት የቀድሞ የሠራዊቱ ድምፅ ስለ ኢፈርትና ሜቴክ በተከታታይ ጹሁፋችን እንደቀረበ ለማመስገን እንወዳለን፡፡ ኢሣት በነዚህ መረጃ አቅራቢዎችን ለምን እንዳላስተናገዱና የመረጃ ምንጩ አስተማማኝ ይሁን አይሁን የሚለው የማምለጫ አብዶ መለኪያው ምን እንደሆነ በግልፅ ካልተቀመጠ ከሃገር ቤት መረጃ የማግኘት ገመዳችሁ ይቆረጣል እንላለን፡፡ ኢሣት አገርቤት ገብቶል፡፡
• የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን ፣የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ወዘተ ህዝባዊ መገናኛ ብዙኃን በመሆን ላበረከቱት አስተዋፆኦ እያመሰገንን፣ አገር ውስጥ ከገባችሁ በሆላ እንደ ማንኛውም የሚዲያ መገኛኛ ብዙኃን የግሉ ዘርፍ፣ በግል፣ ቡድን በአክሲዬን የቴሌቪዝን/ የሬዲዬ ጣቢያ ሆናችሁ መቀጠል እንጂ ህዝብን ገንዘብ አምጡ፣ ነጋ ጠባ መኒ! መኒ! አምጡ ማለት ህዝቡ ለተፈናቃዬች ይርዳ ለእናንተ አስቡበት እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የፌዴራልና፣ የክልል፣ የመንግሥትና የግል የመገናኛ ብዙሃን በምን መልክ መቀጠል ይገባቸዋል ለሚለው ፅንሰ ሃሳብ ተለያዩ ጊዜት ጥናታዊ ዘገባ በማቅረብ በማስረጃ ዘግበናል፡፡ ለዛሬ አጥኝዎች ግብዓት ይሆናል ብለን መጣጥፎቹን ዳግም እናቀርባለን፡፡
• በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እጣ ፈንታ የክልል ዘር ተኮር መንግስቶች ህወኃት/ ብአዴን/ ኦህዴድ/ ደኢህዴን የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በክልላቸው ውስጥ ስውር ሥራዎች በማደራጀትና አንዱ አንዱን በመክሰስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን አጦጡፈውታል፡፡ የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት የጦርነት መጎሰሚያ ሆነዋል፡፡ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደኢህዴድ ባለፈው ጊዜ በየግላቸው አንዳንድ መግለጫዎችን አውጥተዋል። እንዲሁም በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ የክልል ጥያቄ በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ ያስነሳው የድንበርና የወሰን ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ጥያቄ ወዘተ በፅንፈኛ ሚዲያ እየሞቀ እየፈላ መምጣቱ አይቀርም እንላለን፡፡
• በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን፣ የማንነት ጥያቄ ሠለባዎች፣ ባለፉት 27 አመታት ወያኔ ባጸደቀው በዘርና ልሳን በተከለለ ፌዴራላዊ ክልላዊ አስተዳደር የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁም ስቅሉን በማየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በወያኔ ከፋፍለህ ግዛው የአባላህኝ ዘመን ከክልላቸችን ውጡ፣ ቅስቀሳ የተነሳ የሃገራችን ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ግዛት ውስጥ ተዘዋውሮ የመስራት መብቱንና ክብሩን አጥቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንድ ሚሊዩን 500 ሽህ ህዝብ በላይ የኦሮሞና ሱማሌ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በጉጂ ኦሮሞዎችና በሲዳማ ጊዴኦ የዘር ግጭት የተፈናቀሉ ከ750 ሽህ እስከ አንድ ሚሊዮን ወገኞቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በሲዳማና ወላይታ በተከሰተው የዘር ግጭት ከ20 እስከ 30 ሽህ ህዝብ ሲፈናቀል በተመሳሳይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 8510 የትግራይ ተወላጆች የዘር ግጭትን በመፍራት ወደ ትግራይ ክልል ተመልሰዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የትግራይ ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዬን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተደረገ በማለት ከመቐለ በማቅራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ እናቱ የማተችበትም፣ ወንዝ ውሃ ለመቅዳት የወረደችበትም ህፃን እኩል ያለቅሳል እንደሚባለው ዓይነት የኢትዮጵያን ህዝብ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡

• በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ‹‹በፈቃድ ከመጣ ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› (‘No slavery is more disgraceful than that which is self-imposed’Seneca) ይሄ አባባል ለእኛ ‹‹በፈቃድ ከመጣ የልሂቃን ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ቢባል ያስኬዳል፡፡ የኢትዮጵያ ልሂቃን ከባህር ማዶ የቀሰሙትን ትምህርት ከሃገራቸው ተጨባች ሁኔታ ጋር ባለማዛመድ እንዳለ በመቅዳትና በመተርጎም ከስልጣኔ ማማና ከምሁራን ጎራ ቢደመሩም ለሃገራቸው የፖለቲካ፣ ምጣኔ ኃብትና ምህበራዊ ጉዳዮች የሰጡት መፍትሄ አጠያያቂ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በቀኃሥ፣ በደርግና በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ህገ- መንግሥት ከተለያዩ ሃገራት የተገለበጠ ህገመንግሥት፣ የፖለቲካ ርዕዮት፣ የኢኮኖሚ እቅድ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ችግር አፈታት በአጠቃላይ የመንግሥታዊ አስተዳደርና ሥርዓተ መንግሥታዊ መዋቅሮች የተኮረጁና በህዝብ ላይ በግድ የተጫኑ ለመሆናቸው ሾተላይ ሰላይ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በወያኔ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘር ፌዴራሊዝም ፖለቲካ ከተጫነብን 27 አመታት ተቆጠረ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ህዝቡን በልሳን ከፋፍሎ ለሞት፣ እስራት፣ ስደትና መፈናቀል ዳረገው፡፡ በኦሮሞና ሱማሌ፣ በአማራና ትግራይ፣ በሲዳማና ወላይታ፣ ወዘተ በተከሰተው የዘር ግጭት የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች ቁጥር ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን አሻቅቦል፡፡ የህወሃት አመራር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተካሄደበት፣ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመብን ‹ኢንተር ሃሞይ!› ብለው እንደጮሁት ዛሬም ድራማ እየሰሩ ናቸው ታዲያ እነዚህን ቦዘኔ ሌባ የወያኔ አመራሮች ‹‹በፈቃድ ከመጣ የወያኔ አመራር ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ልንላቸው ይገባል፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን ስለማይችል በወልቃይት በራያ ህዝብ ላይ መቐለ የመሸገው ፀረ-ዴሞክራቲክ ኃይል ሚፈፅመው ወንጀል ይዋለወ ይደር እንጂ ለፍርድ መቅረብ አይቀርም እንላለን፡፡ ህወሓት የፈፀመውን ወንጀል፣ አዲስ ወንጀል በማስፈፀም ሊያረሳሳ የሚሞክረው ከንቱ ውዳሴ እንጂ በዚህ በዲጂታል ዘመን የተመዘገበ ማስረጃ አንድ ቀን ፀሃይ ዮሞቀዋል እንላለን፡፡ የ1998ዓ/ም ምርጫ ያጣሩት አንበሶች፣ ዛሬም በዶክተር አብይ መንግሥት ተቀባይነት አጥተው ከሃገር ያለመግባታቸው ሚሥጢር ረቂቅ ነው፡፡ ለዳኛ ፍሬህይወትና ለዳኛ ወልደሚካኤል ዘብ እንደቆሙልን ዘብ ልንቆምላቸው ይገባል እንላለን፡፡

‹‹ከጥንት ጀምሮ እኛ የምናውቀው፣
ሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው፡፡ ባለቅኔ ኃይሉ ገብረህይወት /ገሞራው

• PART I – የኢትዩጵያ ገበሬዎች ትራክተር ከሚገዛ፣ ክላሸን ኮቨ በመቶ ሽህ ብር ይገዛል!!! እንደ መግቢያ
• PART II- ኢትዩ-ቴሌኮምና ቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች! (ክፍል ሁለት) ፊርማው የማን ይሆን!!! የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ Information Network Security Agency (INSA) ቪላድሜር ፑቲንም ኬጂቢ ነበሩ!!! በጥሞና አንብቡት!!! PDF
• PART III- Human Rights Watch “ They Know Everything we do” telecom and internet surveillance in Ethiopia PDF

‹‹የህወሓት/ ኦህዴድ የኢንሣ ጡሩምባ፣ መሬት ቀዶ ገባ!!!››
የኢንሣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!
የህወሓት/ኢህአዴግ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!
ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!

Leave a Reply