ለተፈታኝ ተማሪዎች የጠቅላይ ሚኒስተሩ መልዕክት፦ “የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/nbb0Avk3JwGOBZ4gn0o19SCl8PNN4r9_rwKFt-wCm230Z_x_86PaJfjVxeqZueiSzvgIRzikQqF2Z5JERlXaL0Qg7eUf-auAQBokLH3t0Un5XJzxhBzViCpYy4Id6AStXsCjNQ35o549GtlrIH_RoD4U2C6YGgVLIOFTiHm-Tjyza0HDAs9YE9vitP5J7V6aSqdNAq1ll8mkVhvPLt2wavaIaHm4p9KNOnYTTWoPKuK8LLGrhygJSiqQM6fC7TaAU5ttKBa08GBMMjkEmKWNMXhB0taGPInvXoljXp6pL7pIWwS3p5eOL42kOegiOooXP4i_CoS3BKEQqiiReJ3IiQ.jpg

ለተፈታኝ ተማሪዎች የጠቅላይ ሚኒስተሩ መልዕክት፦

“የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዘንድሮ ተፈታኞቾ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ያሏቸው ተፈታኞቹን፥ “ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት” ብለዋል።

“እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል” ነው ያሉት።

“ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነውም” ብለዋል።

“የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ ሲሉም አሳስበዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ #ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው መግባት እንደማይችሉ መገለጹ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply