ለትራንስፖርት ተገልጋዮች የሚሆን የቦታ ለውጥ ጥቆማ!

የፒያሳ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ድረስ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል፡፡

በተለይም ከፒያሳ ተነስተው ወደ ሃያ ሁለት እና ካሳንቺስ መስመራቸው የነበረ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ከዚህ በኃላ ጣይቱ አካባቢ በተዘጋጀው የስምሪት ቦታ እንዲጠቀሙ መደረጉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትራስፖርት ጽፈት ቤት ሃላፊ አቶ አርጋው በቀለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ መነሻቸው ፒያሳ አድርገው ወደ ካሳንቺስ እና ሃያሁለት የነበረ ተሽከርካሪዎች ጣይቱ ጋር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህ በጊዜያዊነት የተዘጋጀው የስምሪት ቦታ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡

ፒያሳና አካባቢው በተጀመረው አዲስ መንገድ ፕሮጀክት ምክንያት በአካባቢው ያለው የትራንስፖርት አገልግሎት መጨናነቅ እንደተፈጠረ የተናገሩት አቶ አርጋው፣ ትራንስፖርት ቢሮው የከተማ ባሶችን ጭምር በመጠቀም ዜጎች እንዳይጉላሉ እያደረገ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ወደ ካሳንቺስ እና ሃያሁለት መስመራቸው የሆነ ተሽከርካሪዎች ጣይቱ ሆቴል ጋር መነሻቸው አድርገው ወደ እናት ህንጻ በሚወስደው መንገድ አድርገው በዕሪ በከን- ቤተመንግስት- ካሳንቺስ እና ሃያሁለት መሄድ ይችላሉ ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገበርኤል
መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply