ለትግራይ ክልል ከውጭ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ሀገራት በኩል የሚጠበቀው እርዳታ በጊዜ ባለመድረሱ መንግሥት እስካሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ለትግራይ ክልል ከውጭ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ሀገራት በኩል የሚጠበቀው እርዳታ በጊዜ ባለመድረሱ መንግሥት እስካሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ለትግራይ ክልል ከውጭ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ሀገራት በኩል የሚጠበቀው እርዳታ በጊዜ ባለመድረሱ መንግሥት እስካሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ያጋጥማቸው የነበረውን ረዥም የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት በማቃለል አሁን በትግራይ ክልል ለመንቀሳቀስ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ብቻ ዕርዳታውን ለተጠቃሚዎች ማዳረስ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ራቅ ብለው በሚገኙ እና አመቺ ሁኔታ በሌለባቸው የተወሰኑ አከባቢዎችም ጭምር ዕርዳታውን ለማዳረስ በሲቪልና ወታደራዊ በቅንጅት የሚሰራበት ሁኔታ እንደተመቻቸ አሳውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በገለጻቸው እሰከአሁን ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ዕርዳታውን ማድረስ መቻሉ፤ ከተሰራጨው ዕርዳታ ውስጥ 70በመቶ በመንግሰት መሸፈኑን ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ከውጭ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ሀገራት በኩል የሚጠበቀው እርዳታ በጊዜ ባለመድረሱ መንግሥት እስከ አሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ይህን ያህል በጀት መድቦ መንቀሳቀስ በራሱ መንግሥት እርዳታው ለዜጐቻችን እንዲደርስ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ እርዳታ መዘግየት የሚያሳስበው ከሆነ በአፋጣኝ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ እንዲጨምር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚኖርበት አቶ ደመቀ አሳስበዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲጣሩ፤ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከፌዴራል ፓሊስ እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ክልሉ መሰማራቱን ገልፀው፤ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችም ላይ ጭምር ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚፈልግና በዚህ ጉዳይ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በክልሉ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ያለምንም መሸፋፈን ምርመራ እንዲደረግ እና አጥፊዎቹን ለህግ ለማቅረብ መንግሰት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በክልሉ ገብተው በመሬት ላይ ያለውን እውነታ መዘገብ እንዲችሉ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አስረድተዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሙያ ሥነ-ምግባራቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ ግዴታቸው መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

መንግሥት በክልሉ ውስጥ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ሚዲያ እንዲዘግበው እንደሚፈልግ ግልጽ አቋም ያለው ሲሆን በዚህ ረገድ በቅርቡ ታሥረው የነበሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ መደረጉ የዚሁ ቁርጥ አቋም ነፀብራቅ እንደሆነ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት ከላይ የተዘረዘሩትንና ተዛማጅ ችግሮችን ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባራዊ እንቅስቃሴው እያረጋገጠ ባለበት ሁኔታ በመንግሰት ላይ በተደጋጋሚ የሚቀርበው ወቀሳ ተቀባይነት እንደሌለው አስምረውበታል፡፡

መንግሥት የዓለም አቀፍ ህጎችን ጠብቆ የሚሰራ መሆኑን፣ ድጋፍ ለማድረገ ፍላጎት ካላቸው ሃይሎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑንና በቀጣይም ያሉ እና የሚታዩ ክፍተቶችን እንደ አግባቡ ከአጋር አገራትና ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት መፍትሔ ለመስጠት ፍላጎት ያለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በመንግስት ላይ ሀቅን መሰረት ያላደረጉ እና እስከ አሁን የታየውን ከፍተኛ እመርታ ያላገናዘቡ ወቀሳዎች መታረም እንዳለባቸው አሳውቀዋል፡፡ በተመሳሳይም የሀገራችንን ሉዓላዊነትን በመጠበቅ፤ የችግሩ መነሻና እየተደረገ ያለውን ጥረት በመገንዘብ ድጋፍ እየሰጡ ያሉ ሀገሮችንም አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች መንግሥት በክልሉ ያለውን ፈታኝ ሁኔታ ተገንዝቦ አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት በግልጸኝነት እየወሰደ ያላቸውን እርምጃዎች አድንቀዋል፡፡

መንግሥት ላቀረበው ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ጥያቄ በሀገሮቻቸው መንግሥታት በኩል ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ አስፈላጊውን ግፊት እንደሚያደርጉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post ለትግራይ ክልል ከውጭ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ሀገራት በኩል የሚጠበቀው እርዳታ በጊዜ ባለመድረሱ መንግሥት እስካሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.

Source: Link to the Post

Leave a Reply