ለትግራይ ክልል የ3መቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገየስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል የ3መቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።ድጋፉ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና ተጠቃሚነት እንዲ…

ለትግራይ ክልል የ3መቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል የ3መቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና ተጠቃሚነት እንዲሁም በክልሉ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መነቃቃት የሚውል ነዉ ተብሏል፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በፌደራል መንግስትና በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግለትን የትግራይ ክልል ወጣቶች የአቅም ግንባታ የአንድ ማእከል ስልጠናና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን በመቐለ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል።

ሚኒስትሯ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ አካባቢን በማልማት ራስንና ማህበረሰቡን በመጥቀም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ የፌደራል መንግስትና የዓለም ባንክ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት የፌዴራል መንግስትና የዓለም ባንክ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ሚኒስቴሩ ካደረገው ድጋፍም 100 ሚሊዮን ብሩ ለክልሉ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም 200 ሚሊዮን ብር ደግሞ በክልሉ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማነቃቂያ እንደሚውልም ተገልጿል።

ድጋፉ የክህሎት ስልጠና እየተሰጣቸው ለሚገኙ ሁለት ሺሕ ወጣቶች በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ የመነሻ ካፒታል እንደሚሆናቸው በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ ገነት አረፈ መግለጻቸውን ሰምተናል ።

ልዑል ወልዴ

ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply