ለአመታት ሳይወገድ ተከማችቶ የነበረ አደገኛ ኬሚካል መወገዱ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢኒስቲትዩት እንዳስታወቀው ተከማችቶ የነበረ 95 በመቶ አደገኛ ኬሚካል ማስወገዱን አመላክቷል:: ተ…

ለአመታት ሳይወገድ ተከማችቶ የነበረ አደገኛ ኬሚካል መወገዱ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢኒስቲትዩት እንዳስታወቀው ተከማችቶ የነበረ
95 በመቶ አደገኛ ኬሚካል ማስወገዱን አመላክቷል::

ተቋሙ ያስወገደው አደገኛ ኬሚካል በእንስሳትና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ እንደነበረ ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ጂዮሎጂካል ኢንስታትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጀራ ተስፋዬ እንደተናገሩት ለአመታት ኬሚካሎች ሳይወገዱ ተከማችተው በመቆየታቸው ምክንያት ስጋት ፈጥሮ መቆየቱን ተናግረዋል።

ተወገዱ ያሏቸውን የኬሚካል አይነቶች ግን በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

በሌላ በኩል ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አደገኛ ኬሚካሎቹ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እና ለማስወገድ በባለሙያዎች የተዘረጋው የአሰራር ስርዓት እየተተገበረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሔኖክ ወገብርኤል

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply