ለአመታት የዘለቀው የማረቆና መስቃን ግጭት በእርቀሰላም ሊቋጭ መሆኑ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ መካከል ለአመታት የዘለቀዉ ግጭት ለአንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት በነገው እለት እርቀሰላም ሊካሔድ መሆኑ ተነግሯል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ህዝቦች መካከል ለአመታት የዘለቀዉ አለመግባባት በነገዉ እለት በእርቀሰላም ለመቋጨት ዝግጅት መደረጉ ክልሉ አስታውቋል።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ወንድማማች በሁኑ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት መሆን ያልነበረባቸው እና መከሰት ያልነበረባቸው ክስተቶች ተከስተው ህዘቡ በሰላም እጦት እንዲቆይ አድርጓል ብለዋል።

ነገ በሚደረገው እርቀሰላም የሁለቱም ህዝቦች እንደሚሳተፋም ነግረውናል።

በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው 27 ሰዎች ተይዘው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ ሲሉ ሃላፊው ለጣበያችን ተናግረዋል።

ለህዝቡ የግጭት ምክንያት የሆኑ ለዘመናት የተከማቹ ጥያቄዎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ተመስገን ወደ ግጭት ሳያመሩ በምክክር ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply