ለአማራ ህልውና በደባርቅና አካባቢዋ ለተሰው የጀግኖች ቤተሰቦች ከ300 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ…

ለአማራ ህልውና በደባርቅና አካባቢዋ ለተሰው የጀግኖች ቤተሰቦች ከ300 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ለሀገር ሠላም ሲሉ ቤተሰባቸውን ጥለው አሸባሪውን ህወሓት ለመቅበር መስዋእት የከፈሉ የ65 ጀግና ቤተሰቦችን አንድነት ለመላው አማራ የደባርቅና አካባቢዋ የመረዳጃ ማህበር 325ሺ ብር ድጋፍ አድርጓል። የደባርቅ ወረዳ ዋና አተዳዳሪ አቶ ሰላምይሁን ሙላት ለህውና ዘመቻው መንግስትና ህብረተሰቡ ባደረገው ተጋድሎ አሁን ያለውን አየር እንድተነፍስ አድርጎናል ብለዋል። በደባርቅና አካባቢዋ በተፈጠሩ አውደ ውጊያዎች መስዋዕትነት ከፍለው ሠላም ያመጡትን ጀግኖች አድንቀዋል። በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የደባርቅና አካባቢዋ ተወላጅ የውጭ ሀገር ነዋሪዎች ከሚሠሩት በመቀነስና ሀብት በማሰባሰብ ኮሚቴ ተዋቅሮ ለተቸገሩ መድረስ ትልቅ መስዋእትነት እንደሆነም ተናግረዋል። ይህን የተቀደሰ ተግባር ለፈጸሙት በሙሉ በወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት ስም ላቅ ያ ምስጋና አቅርበዋል። ገነት ጥላየ የአንድነት ለመላው አማራ የደባርቅና አካባቢዋ የመረዳጃ ማህበር ሰብሳቢ ሲሆኑ ከሐምሌ 05/2013ዓ.ም ጀምሮ ለህልውና አደጋ ሆኖ የቆየው ይህ ጦርነት የሠብዓዊ ቁሳዊ ወድመት አስከትሏል ብለዋል። ይህንን መሠረት በማድረግ ማህበር ተመሥርቶ ካለው ጉዳት የከፋው መስዋትነት መክፈሉ የበለጠ በመሆኑ በህልውና ዘመቻው ለተሰው የ65 ጀግኖች ቤተሰቦች ለእያንዳንዱ 5,000 ድጋፍ እጅ በጅ መደረጉን አስረድተዋል። ማህበሩ በዚህ የሚቆም ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ነው ብለዋል። የደባርቅ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አየልኝ ክብረት የዚህ መረዳጃ ማህበር ኮሚቴ ናቸው። የደባርቅንና አካባቢዋን መወረር የሚያማቸው የውጭ ወገኖች ለህጻናት ደብተር፣ ለቡናና ለቁርስ ይሆን ዘንድ ለተሰውት ቤተሠቦች ለማድረስ እንደተላከ አብራርተዋል። የመጣውን ገንዘብ በአግባቡ በመጠቀም ለቁም ነገር ማዋል እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል። በመጠረሻም በህልውና ዘመቻው አባቷን ያጣችው የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሽዋነሽ ዋቢ የቦዛ አብርሃም ቀበሌ ነዋሪ ናት። አስተማሪዋን፣ አሳዳጊዋን አባቷን ማጣት ቢከብድም ሀገር ሲወረውር ዝም ብሎ ሳይመለከት ጠላትን ከመጣበት ሳይወጣ ቀብሮ እንዲቀር ድርጎ በመሰዋቱ ኩራት ይሰማኛል፤ በወገኖቻችን መዘከሩ አባቴ አልሞተም በታሪክ ህያው ነው ብላለች። በዛሬ እለት የተደረገውን ድጋፍ አመስግና ለተሰውት በሙሉ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የማቋቋም ሥራ ቢሠሩልን ስትል ጠይቃለች ሲል የደባርቅ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply