
“ለአማራ ህዝብ የተከፈለ የልጅ ናፍቆት ፣ፍቅር እና እናትነት!” የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ሰኔ 27/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መምህርት ፣ጋዜጠኛ እና ፀሐፊ የሆነችው መስከረም አበራ ሁለት ጨቅላ ህፃናትን ይዛ ነው ለአማራ ህዝብ ድምፅ የሆነችው ። በበሰለና በሰላ ፖለቲካ ትንታኔ ፣በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃና መረጃ በመያዝ ነው ይህንን ፋሽስታዊ ስርዓት የሞገተችው ። መስከረም ልጆቼን ዝም ብዬ ላሳድግ ሳትል የፋሺስቱ የኦህዴድ ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል መቆም አለበት ብላ ተሟገተችው ፥ታገለችው ። በአሁኑ ወቅት እምቦቀቅላ ልጆቿን ፣የእናታቸውን ፍቅር ፣እንክብካቤና ድጋፍ የሚሹ ከጨቅላ ልጆቿ ተለይታ ፤ ከበርካታ የአማራ ምሁራን ፣ጋዜጠኞች ፣የሲቪክ ማህበራት መሪዎች ጋር በአገዛዙ በግፍ እሰር ላይ ትገኛለች ። ልጆቿም የእናት ፍቅር ፣እንክብካቤ እና ድጋፍ አጥተዋል። የአማራ ወጣቶች ማህበር እየከፈልሽ ላለሽው ፣ለከፈልሽው ታላቅ መስዕዋትነት ልባዊ ክብር አለው ። ታሪክሽ በአማራ ህዝብ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ቦታ አለው። አማራዊ ገድልሽ በደማቁ ይፃፋል። በተጨማሪም አማራ በመሆናችሁ በፋሽስቱ አገዛዝ በግፍ እስር ላይ ለምትገኙ የአማራ መሪዎች ፣ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች ለከፈላችሁት መስዕዋትነት ታላቅ ክብር አለን። የአማራ ህዝብ ትግል የህልውና አደጋን መቀልበስ ነው ። ትግላችን እጅግ ፍትሃዊ ፣ሞራላዊ እና ግዴታ ነው ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል!!
Source: Link to the Post