ለአማራ ተማሪዎች ቀጣይ የደህንነት ህልውና ሲባል ጠንካራ ዘመቻ ማድረግ እንደሚጠይቅ የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ አመራሮችና ደጋፊዎች ገለፁ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013ዓ.ም…

ለአማራ ተማሪዎች ቀጣይ የደህንነት ህልውና ሲባል ጠንካራ ዘመቻ ማድረግ እንደሚጠይቅ የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ አመራሮችና ደጋፊዎች ገለፁ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ተማሪዎች በሀገሪቱ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ከአሁን በፊት የተቀበሉትን ያልተገባ መከራ ታሳቢ ያደረገና የተደቀነባቸውን የወደፊት ችግር ለመጋፈጥ ጠንከር ያለ ዘመቻ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ አመራሮችና የማህበሩ ደጋፊዎች ገልጸዋል፡፡ የአማራ ተማሪዎች በተለይ ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያልተገባቸውን ፈተና ሲቀበሉ ቆይተዋል ያሉት አመራሮቹ በቀጣይ እንዳለፉት አይነት ችግሮች በአማራ ተማሪዎች ላይ እንዳይፈጸም በትኩረት መሰራት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ የአማራ ተማሪዎች በዘመቻ ሚኒሊክ የአንድ ደርዘን ደብተር ፤እስክርቢቶ እና አንድ መጽሀፍት መርሀ ግብር ላይ ላቅ ያለ ተሳትፎ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ከተገኙት የማህበረሰብ አንቂዎች መካከል ቶማስ ጀጃው ሞላ ሁላችንም በንቃት የአማራ ተማሪዎችን ከጥቃት ለመታደግ መታተር አለብን ብለዋል፡፡ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አለሙ አራጌ አሁን ላይ በአማራ ተማሪዎች ላይ የተከፈተው የጥቃት ዘመቻ በቀጣዩ የአማራ ማህበረሰብ ዘንድ የትውልድ ክፍተት ለመፍጠር ያለመ ረጅም ርቀትን ያነጣጠረ የጥቃት ስልት ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ጋዜጠኛ መዓዛ ማህመድ ባለፈው ጊዜ በአማራ ተማሪዎች ላይ የጠፈጸመውን ጥቃት መንግስት በውል ለይቶ ማመን ካልቻለ ጥፋቱ ይቀጥላል የሚል ስጋቻ አለኝ የሚል ሀሳብ ሰንዝራለች፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply