ለአማራ ክልል አመራሮች!! በአበው ብሂል አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛም ይባል ነበር። የምትመሩት ህዝብ እንደት እና በምን ሁናቴ ላይ እንዳለ ለማወቅ ምን ተስኗችሁ ይሁን?? ~~~~~~ አሸና…

ለአማራ ክልል አመራሮች!! በአበው ብሂል አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛም ይባል ነበር። የምትመሩት ህዝብ እንደት እና በምን ሁናቴ ላይ እንዳለ ለማወቅ ምን ተስኗችሁ ይሁን?? ~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~~ የአማራ ህዝብ በሚኖርባት እናት ሃገሩ #ባይተዋር መሆኑንስ አላወቃችሁምን?? የአማራ ህዝብ ጥሮ ግሮ ባፈራው ሃብቱ ማዘዝ ከተሳነው ሰንበትበት ማለቱን አልሰማችሁምን?? የአማራ ህዝብ በሁሉም አካባቢ በሚባል ሁናቴ በሚኖርበት የራሱ ክልል ጭምር መዋቅራዊ ጥቃት አልደረሰበትንም?? ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል?? አማራነት እጅግ ዋጋ የሚያስከፍል ማንነት ሆኗል። ሰዎች መርጠው ባልተወለዱበት ሃገር ተመርጠው ይገደላሉ፣ይፈናቀላሉ፣ይዘረፋሉ …… እናንተ ግን የት ናችሁ?? ለማንኛውም አማራነት ከፈጣሪ በታች #አዳኝ ከለላ፣መከታ እና ጠበቃ የለውም። የእውነት አምላክ ግን ጊዜውን ጠብቆ ፍርድ ይሰጣል። ግደለም እግዚያብሄር መልስ አለው። የምናምነው የድንግል ማሪያም ልጅ እንደ እኛ ሳይሆን እንደ እርሱ በጊዜው ይመለሳል ብለን ተስፋም እናደርጋለን። እናንተ አመራሮች ግን የት ናችሁ?? መልሱን በራሳችሁ ሚዛን መልሱት …!!! አማራው ግን በእናንተ በመሪዎች አፍሯል። በሰነፍ መሪዎች የተከበበ ጠንካራ ህዝብ ይዛችሁ በጠላት አስደብድባችሁታል፣ቃላችሁን ክደችሁታል፣ሃብት ንብረቱን አስዘርፋችሁታል፣ከተሞቹን አወድማችሁበታል፣ ታድያ ይሄ ሁሉ ነገር የተፈፀመበት ህዝብ መሪ አለውን ?? እናንተስ አለን ትላላችሁ?? ስለሆነም ህዝባችን ከትናንቱ የቀጠለ አፓርታይድ ስርዓት ሰልችቶታል።አሁን በሚገባው ልክ ፍትህ፣ልማት ፣ሰላም እና ድሞክራሲን ይሻል። እናንተም ከነበራችሁ የተቸነከረ ፓለቲካዊ አስተሳሰብ ወጥታችሁ የህዝብ ደጀን እንድትሆኑ እንፈልጋለን።ትላንት ወያኔ ህዝባችንን የጨፈጨፈበት ሰውሰራሺ ድርጊት አሁንም እንዳይደገም የጥንቃቄ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል። ህዝባችሁን የምትክሱበት ጊዜው አሁን ነው። ከዚህ በዘለለ አአ አትገቡም የሚል ስርዓትን ለማስቀጠል እና በአማራ ህዝብ ላይ ተጨማሪ ኪሳራ መመደብ ይቁም። አማራነት ወንጀል ከሆነ እናንተም ከህዝባችን ጫንቃ ላይ ውረዱ። ህዝባችንን በፎቶ ፓለቲካ እና በድርብርብ አጀንዳዎች ማታለሉ ይብቃ። የወሎን ህዝብ ከርስት ማንነቱ በመነጠል የሚቀጥል የብልፅግና ስርዓትም አይኖርም። የአማራ ህዝብን አሳልፎ የመሰጠት ፓለቲካ ዘመኑን የዋጀ አካሄድ አይደለም።መሰረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ያ ዘመን ፋሺን ሆኖ አልፏል። አማራነትን ለመናኛ ጥቅም እየተጠቀሙ በማያተርፍ መንገድ መጓዙ ዋጋችሁን አርክሶታል። የአማራ ህዝብ ነባር ባህሉን እያናወጠው እና ቅርፁን እየደመሰሰው ያለው ብአዴናዊ አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ መክሰም ባለመቻሉ ነው። ስለሆነም የአማራ ህዝብ መሪዎች እባካችሁን ከአጀንዳ ተሸካሚነት እና ከአንጋሺነት ውጡ። አማራም እኮ ጠ/ሚ/ር መሆን ይችላል። ይሄው ነው!!! © አሸናፊ ገናን ስቶክሆልም :- ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply