ለአራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አለሁ እንበል!የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳትን ለማጠናቀቅ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ ታላቅ ጉባኤ በትናንትናው እለት ተጀምሯል፡፡በጉ…

ለአራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አለሁ እንበል!

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳትን ለማጠናቀቅ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ ታላቅ ጉባኤ በትናንትናው እለት ተጀምሯል፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የካቴድራሉን ህንጻ ዕድሳት አሁናዊ የጥገና ሥራ እና ለዚሁ ካቴድራል እድሳት የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ተሰጥቷል።

በመርሐግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ፣ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

ከትናንት ጀምሮ እስከ ሰኔ 7 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ላይ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የቀጥታ ስርጭቱን በመከታተል አቅማቸው የፈቀደውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በ1924 በኢትዮጵያው ንጉሰ ነገስት በአጼ ይለ ስላሴ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ ስራው ቢጀመርም ጣሊያን ሃገራችንን በመውረሯ ግንባታው ሊቋረጥ ችሏል፡፡ እንደገና ከድል በኋላ በ1936 ዓ.ም ህንጻውን አጠናቀው በይፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ከተደረገ ወዲህ ካቴድራሉ በዘላቂነት ሊያቆይ የሚችል ጠንካራና ሁለንተናዊ እድሳት ሳይደረግለት ቆይቷል፡፡

በዚህም ምክንያት የህንጻው ጣራ እያፈሰሰ፣ ግድግዳው እየፈረሰና የተለያዩ ጉዳቶች እየደረሰበት በመገኘቱ በ172 ሚሊዮን ብር የሥራ ውል ሥምምነት ተደርጎ ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡

በዚህም አጠቃላይ የህንጻ ጥገና ስራዉ 83 በመቶ የተከናወነ ሲሆን ቀሪ ስራውን ለማጠናቀቅም ከ85 እስከ 90 ሚሊዮን ብር እንደሚጠይቅ ታውቋል፡፡

በመሆኑም የጀመርነውን ማጠናቀቅ ይገባልና አሁንም ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስፈልገውን ወጭ ለማሟላት ከትናንት ጀምሮ እስከ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም የሚቆይ የቀጥታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ስለተዘጋጀ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለእድሳቱ ድጋፍ ለማድረግ፡-
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ -1000003778634
በአቢሲኒያ ባንክ-53431186
በአዋሽ ባንክ-01320414050300
በንብ ባንክ-7000022335516
በአባይ ባንክ-9521119824771019
ወይም በሁለም ባንኮች 7829 ገቢ በማድረግ የታሪኩ አካል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

ጎ ፈንድ ሚ-
https://www.gofundme.com/f/wkn6c4
ወገን ፈንድ:- https://www.wegenfund.com/causes/holytrinity/
በካቴድራሉ ዌብሳይት :- https://eotc-htc.org
ለበለጠ መረጃ: 0911243871/ 0988202727 / 0923256051/ ይደውሉ፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ በካቴድራሉ ሚዲያ እንዲሁም በራማ ቲዩብ ፣በቋንቋዬነሽ ሚዲያ፣በነጋሽ ሚዲያ፣በመንክር ሚዲያ፣በ21 ሚዲያ፣ በንቁ ሚዲያ እና በተለያዩ የዩቲዩብና የቴሌቭዥን ቻናሎች እየተላለፈ ይገኛል።

ለአራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አለሁ እንበል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply