ለአርበኛ ፋኖ አጋየ አድማስ የመኖሪያ ቤት ስጦታ ተበረከተለት። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት በግንባ…

ለአርበኛ ፋኖ አጋየ አድማስ የመኖሪያ ቤት ስጦታ ተበረከተለት። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት በግንባር ከፍተኛ ተጋድሎ እየፈጸመ ለሚገኘው አርበኛ አጋየ አድማስ የመኖሪያ ቤት ተበረክቶለታል። የጎንደር ከተማ ዞብል ክፍለ ከተማ ነው ለአርበኛ ፋኖ አጋየ አድማስ የመኖሪያ ቤት ስጦታ ያበረከተለት፡፡ ክፍለ ከተማው የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ለፋኖ አጋየ አድማስ ቤተሰቦች አስረክቧል። የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አወቀ አስፈሬ በቁልፍ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት÷ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ጦርነት መሰረት አድርጎ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በብርቱ እየተፈለሙት ነው። አርበኛ ፋኖ አጋየ አድማስም በግንባር ቀደምትነት ቤተሰቦቹን ትቶ በመዝመት ጠላትን እየተዋጋ ይገኛል ያሉት ሃላፊው÷ እሱን አለማበረታት እንደ ንፉግነት ይቆጠራልም ብለዋል። የዞብል ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብረሚካኤል አየልኝ ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት ለመታደግ በግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ለሚገኝው ፋኖ አጋየ አድማስ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው የክፍለ ከተማው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መወሰኑን ገልጸዋል። የአርበኛ ፋኖ አጋየ እናት ወይዘሮ ሀብታም መኮንን በበኩላቸው÷ልጄ ለሀገር እየከፈለ ያለውን ዋጋ በሚገባ ተረድታችሁ ይህንን ስጦታ በማበርከታችሁ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል። ለኢትዮጵያ ባለውለታዎች በቀጣይ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረጉ እንደሚቀጥል ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። ፋኖ አጋየ አሸባሪ ቡድኑ አማራ ክልልን ከወረረ ጀምሮ በግንባር የተለያዩ ጀብዶችን እየፈጸመ ይገኛል። ጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply