ለአርቲስት ማሪቱ ለገሰ በኮምቦልቻ ከተማ በስሟ ጎዳና ተሰየመላት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ክብር ዶክተር አርቲስት ማሪቱ ለገ…

ለአርቲስት ማሪቱ ለገሰ በኮምቦልቻ ከተማ በስሟ ጎዳና ተሰየመላት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ክብር ዶክተር አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከረጅም ዓመታት የአሜሪካ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢዋ ወሎ ገብታለች። ለተወዳጇ አርቲስት ማሪቱ የተሰየመው መንገድ ከልዑል መኮነን ሆቴል ወደ ኤር ፖርት የሚወስደው መንገድ ነው። ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ በኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሀመድ አሚን የሱፍና የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በከተማው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ አካላት፣ ቤተሰቦቿ፣ የሙያ አጋሮቿ እንዲሁም አድናቂዎቿ ደማቅ አቀባበል አድርገውላታል። ተወዳጇ አርቲስት ማሪቱ በኢትዮጵያ ቆይታዋ አዲስ አልበሟን ለአድናቂዎቿ ታቀርባለች። በደሴ፣ ጎንደርና ባህር ዳር ከተማዎች የሙዚቃ ሥራዋን ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የወሎ ዩኒቨርስቲ ከ7 ዓመት በፊት ያበረከተላትን የክብር ዶክትሬት ለአርቲስቷ በአካል እንደሚያበረክት ከኮምቦልቻ ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል አማራ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply