ለአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ለአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ይህ የተባለው በዝክረ አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ነው፡፡

የሙዚቃ ኮንሰርቱ በሸገር ወዳጅነት ፓርክ ውስጥ ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡

ኮንሰርቱ “ቆሜ ልመርቅሽ” በሚል በአልበሙ መጠሪያ ነው የተሰየመው፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአርቲስቱ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ህያው እንዲሆን ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

የመሰረት ድንጋዩ ከሸራተን ሆቴል ፊትለፊት እንደተቀመጠም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ለአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply