ለአስከሬን እንኳ ክብር የተነፈገበት የሸዋሮቢቱ መንግስታዊ ነውር እንደቀጠለ ነው! ስቶክሆልም :- ሰኔ 26/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ “ህግ-ማስከበር” ማለት ወ…

ለአስከሬን እንኳ ክብር የተነፈገበት የሸዋሮቢቱ መንግስታዊ ነውር እንደቀጠለ ነው! ስቶክሆልም :- ሰኔ 26/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ “ህግ-ማስከበር” ማለት ወንጀለኛ ወይም በወንጀል የተጠረጠሩትን አካላት በሀገሪቱ ህግና የህግ አፈፃፀም ስነ-ስርአት በመረጃና በማስረጃ ክስ መስርቶ ፍትህ ማስፈን እንጂ መንግስታዊ ነውርና ፍጅት መፈፀም አይደለም፡፡ በሸዋሮቢት የተፈፀመውና አስከሬን እንደማገዶ እንጨት ተጭኖ በከተማ መሀል የዞረበት ድርጊት በአምልኳዊም ሆነ በሰብአዊ እይታ ትልቅ ነውር ነው፡፡ በህግም ያልተገባ ድርጊት ነው፡፡ እስካሁን በሸዋሮቢት 8 ወጣቶች ተገድለው አስከሬናቸው ሳይቀር ተንገላቶ ቀብራቸው ተፈፅሟል፡፡ 5 ወጣቶች በፅኑ ጉዳት ሪፈር የተባሉ ሲሆን በአካባቢው የጤና ተቋማት በህክምና ላይ ያሉ ደግሞ ወደ 12 ደርሰዋል፡፡ በግርግሩ በአጠቃላይ ወደ 100 ሰዎች ቀላል ጉዳት አስተናግደዋል፡፡ የታሠሩትንና ታፍነው የደረሱበት ያልታወቁትን በተመለከተ ደግሞ የአብን የሸዋሮቢት ና ቀወት ወረዳ ሰብሳቢ ያሬድ ሙሉነህ እና አዶናይ አበበ የተባለ አባል ሲታሰሩ ፥ ከወጣቶች በአጠቃላይ እስካሁን 17 ወጣቶች ታስረዋል ፤ 2 መምህራን ታፍነው የደረሱበት አይታወቅም እንዲሁም ሌሎች ያልታወቁ አድራሻቸው የጠፋ ወጣቶች መኖራቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል፡፡ በህግ-ማስከበር ሽፋን ህዝብን አንገት የሚያስደፋና ለሞራል ተቃራኒ የሆነ ግፍ መፈፀም በአስቸኳይ ይቁም! © ዘሪሁን ገሠሠ #sayenouph #Stopa_Amhara_Genocide #StopAmharaGenocide #በቃን #AmharaGenocide #እምቢ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply